የሰው ልጅ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እያደረገ ያለው ጥረት በቂ እንዳልሆነ ተገለጸ
የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ከተቀረጹ መንገዶች ውስጥ እየተተገበሩ ያሉት 20ዎቹ ብቻ ናቸው ተብሏል
ምድራችን በ100 ዓመት ታሪክ ውስጥ በተያዘው ዓመት ከፍተኛውን ሙቀት ማስመዝገቧ ይታወሳል
የሰው ልጅ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እያደረገ ያለው ጥረት በቂ እንዳልሆነ ተገለጸ።
የአሜሪካው ባዮ ሳይንስ የምርምር ኢንስቲትዩት ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ጥናት መሰረት የሰው ልጆች የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት የሚጠበቅባቸውን ያህል እየሰራ እንዳልሆነ ተገልጿል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት 35 የተዘጋጁ ዓለም አቀፍ የመፍትሔ እርምጃዎች ተለይተው ነበር ተብሏል።
ይሁንና የሰው ልጆች እየተገበራቸው ያሉት እርምጃዎች 20 ዎቹ ብቻ ናቸው የተባለ ሲሆን ይህም ምድር ለሰው ልጆች ህይወት ምቹ እንዳትሆን እያደረጋት እንደሆነ ተገልጿል።
ምድራችን በ100 ዓመት ታሪክ ውስጥ በተያዘው 2023 ዓመት ከፍተኛውን ሙቀት ያስመዘገበችው የሰው ልጆች የሚጠበቅባቸውን ያህል እየሰሩ ባለመሆኑ ነውም ተብሏል።
የእሳት ቃጠሎ መከሰት፣ ድርቅ፣ ከፍተኛ ቅዝቃዜ፣ የውሀ መጥለቅለቅ እና የመሬት መንሸራተት ደግሞ እየተከሰቱ ካሉ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎች ናቸው።
ካናዳ በተያዘው ዓመት በተከሰተ ሙቀት ምክንያት የእሳት አደጋዎችን በስፋት ካስተናገዱ ሀገራት መካከል እንዷ ስትሆን 45 ሚሊዮን ደን ተቃጥሎባታል ተብሏል።
ቻይና፣ ሊቢያ፣ ሕንድ እና አሜሪካ ደግሞ የግግር በረዶ በመቅለጡ ምክንያት የውሀ መጥለቅለቅ አደጋ ያጋጠማቸው ሀገራት ሆነዋል።
በአጠቃላይ የሰው ልጅ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከያ መንገዶችን ባለመጠቅሙ ምክንያት ምድር ለሰው ልጆች እንዳትትመች ማድረጉን በኦሪጎን ዩንቨርስቲ የአካባቢ ጥበቃ ተመራማሪው ዊሊያም ሪፕል ተናግረዋል።