ኢኮኖሚ
ግብጽ ለማህበራዊ ዋስትና የሚውል የግማሽ ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ከአለም ባንክ አገኘች
እንደ ባንኩ ከሆነ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ግብፃውያን ከድጋፉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
ባንኩ ግብጽ ለምታከናውነው የማህበራዊ ዋስትና ኘሮግራም የ500 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማጽደቁን አስታውቋል
የአለም ባንክ ግብጹ ለምታከናውነው የማህበራዊ ዋስትና ኘሮግራም የ500 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማጽደቁን አስታውቋል።
የአለም ባንክ ድጋፉን ያደረገው አለም አቀፍ የሆነ የኢኮኖሚ ጫና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ በሚያደርሰው ጫና በመጨመሩ ምክንያት መሆኑን ገልጿል
ገንዘቡ መንግስት በ2015 ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመረውን የታካፉል እና ካራማ ቅድመ ሁኔታዊ እና ቅድመ ሁኔታ የሌለውን የገንዘብ ዝውውር መርሃ ግብር የሚደግፍ ነው ብሏል ባንኩ።
እንደ ባንኩ ከሆነ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ግብፃውያን ከድጋፉ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
መርሃ ግብሩ ከተጀመረበት ከፈረንጆቹ 2015 ጊዜ ጀምሮ 900 ሚሊዮን ዶላር ፈንድ አግኝቷል፤ በዚህም 12 ነጥብ 8 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች እንዲጠቀሙ አስችሏል።
ግብጽ ከአረቡ አለም በህዝብ ብዛት ቀዳሚ ነች።