ህንድ ደግሞ ቻይናን ተከትላ ሁለተኛውን ደረጃ ትይዛለች ተብሏል
የአሜሪካው ኢንቨስትመንት ባንክ ጎልድማን ሳችስ የ2075 የአለም ኢኮኖሚ ምን እንደሚመስል ትንበያውን አጋርቷል።
በዚህም መሰረት ቻይና ቀዳሚውን ደረጃ ስትይዝ፥ ህንድ አሜሪካን በመቅደም የአለማችን ሁለተኛውን ግዙፍ ኢኮኖሚ ይኖራታል ብሏል ባንኩ።
በዚህ አመት የአለማችን ባለብዙ ህዝብ ሀገር መሪነትን ከቻይና የተረከበችው ኒው ደልሂ፥ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በኢንቨስትመንት ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበች ነው።
በአፍሪካ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት ናይጀሪያም በቀጣይ 52 አመታት በአለማችን አምስተኛዋ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ሀገር ትሆናለች ነው ያለው ጎልድማን ሳችስ።
ኢትዮጵያም በ6 ነጥብ 2 ትሪሊየን ዶላር 17ኛ ላይ እንደምትቀ ነው ትንበያው ያመላከተው።
በ2075 ፈርጣማ ኢኮኖሚ የሚኖራቸው 10 ሀገራት የትኞቹ ናቸው? የሚለውን በቀጣዩ ምስል ይመልከቱ፦