ዓለም አማራጭ የኢኮኖሚ ልማት ሞዴሎችን እየፈለገች ነው ተባለ
የፓሪሱ የዓለም የገንዘብ ጉባኤ አዲሱ ምዕራፍ የሚከፍት ጉባኤ እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል
ዓለም ቻይና ያቀረበችውን አማራጭ የኢኮኖሚ ልማት ለማጥናት ጊዜው አሁን ነው ተብሏል
በጄኔቫ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር የሆኑት ጊልስ-ኢማኑኤል ዣክ በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ የተጀመረው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ስምምነት የመሪዎች ጉባኤ በአማራጭ የኢኮኖሚ ልማት ሞዴሎች ላይ ለመወያየት እድልን ይሰጣል ብለዋል።
ባለሞያው ለአል ዐይን ኒውስ ቻይናን በመጥቀስ፤ ሀገሪቱ ቀደም ሲል ያቀረበችውን አማራጭ የኢኮኖሚ ልማት ለማጥናት ጊዜው አሁን ነው ብለዋል።
የጉባኤው ዓላማ እ.አ.አ. በ1944 የዓለም ባንክንና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ፈንድን የወለደውን ስምምነት ለማደስ ነው።
በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ከሁለቱ ተቋማት ገንዘብ ማግኘት አስቸጋሪ ነው ይላሉ። ሆኖም የሙቀት ማዕበልን፣ ድርቅንና ጎርፍን እንዲሁም ከቅሪተ አካል ነዳጅ በመውጣት ተፈጥሮን በመጠበቅና ከድህነት ለመውጣት ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው።
በዚሁ አውድ ዣክ ስብሰባውን "የምዕራባውያን ሀገሮች በልማት መስክ ዓለም አቀፋዊ የፋይናንስ ስርዓት አመራርን ለማስቀጠል የሚሞክሩበት አጋጣሚ ነው" ብለውታል።
"ጉባኤው በአብዛኛዎቹ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ውስጥ ከገቡት ቁርጠኝነት አንጻር የሚታይ ነው" ሲሉ አብራርተዋል።
በሚቀጥለው ህዳር በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በዱባይ ቀጠሮ የተያዘለትን ጉባኤ ተስፈኝነታቸውን ገልጸዋል።
በግብጽ የተካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 27) ላይ የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ማትሌይ ያቀረቡት በድሀ ሀገሮች መካከል የነበረው የአየር ንብረት ድርድር እንቅፋት መሻሻሎችን የመመልከት ተስፋ መፈጠሩ ትኩረት የሚስብ ነው።
ሀብታም ሀገራት የግሪን ሀውስ ጋዝ ልቀቶች ዋና መንስኤ ናቸው።
በጉባኤው ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ፣ የጀርመን መራሂተ መንግስት ኦላፍ ሾልስ እና የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት የለን ተገኝተዋል።