ጠ/ሚ ዐቢይ ኢትዮጵያ በዘንድሮው ዓመት 6 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገቧን ገለጹ
የኢትዮጵያ ዕዳ ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ምርት የ38 በመቶ ድርሻ እንዳለውም ጠ/ሚኒስትሩ አስታውቀዋል
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ በዘንድሮው ዓመት 6 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገቧን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ለጠቅላይ ሚንስትሩ ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል የስራ አጥነት፣ የኑሮ ውድነት፣ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት፣ የነጋዴዎች ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ ለመስራት መቸገር እና ሌሎችም ዋነኞቹ ናቸው።
ለጠቅላይ ሚንስትሩ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ከመጋቢት 2010 ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ በኑሮ ውድነት፣ በስራ አጥነት እና በግብዓት ዕጥረት እየተጎዳ መሆኑን መንግስትስ እነዚህ ችግሮች ለመፍታት ምን እየተሰራ ነው የሚሉት ዋነኞቹ ናቸው።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በምላሻቸውም አሁን ያለው ዋጋ ንረት 30 በመቶ ነው ብለዋል።
የዋጋ ግሽበቱን አሁን ካለበት በሚቀጥለው አመት ለመቀነስ እንሰራለን ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ መንግስታቸው በተያዘው ዓመት ለነዳጅ ድጎማ 77 ቢልየን ብር ወጪ ማድረጉን ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ቢያንስ 6 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ማስመዝገቧን የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትሩ በ2016 ዓመት ዱግሞ የ6 ነጥብ 4 በመቶ እድገት ታስመዘግባለች ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለውም የኢትዮጵያ ዕዳ ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ምርት ( 6 ነጥብ 2 ትሪሊየን ዶላር) የ38 በመቶ ድርሻ አለውም ብለዋል።
የሀገር ውስጥ ባንኮች 461 ቢልየን ብር ብድር ሰትተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከዚህ ውስጥ 85 በመቶው ለግል ባለሀብቶች የተሰጠ እንደሆነ ተናግረዋል ።
የሀገር ውስጥ ባንኮች አጠቃላይ ሀብት 2 ነጥብ ዘጠኝ ትሪልየን ብር መድረሱንም ጠቅላይ ሚንስትሩ በምላሻቸው ወቅት ጠቅሰዋል።
በመጠናቀቅ ላይ ባለው በጀት ዓመት 15 ቢልየን ዳላር ዋጋ ያለው ምርት ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል የተባለ ሲሆን የወጪና የገቢ ሚዛኑ ከ13 በመቶ ወደ 9 ነጥብ 8 በመቶ ቀንሷል ተብሏል።
ኢትዮጵያ እስከ ግንቦት 30 ድረስ ባሉት 11 ወራት ወደ ውጭ ሀገራት ከላከቻቸው ምርቶች 4 ነጥብ 6 ቢልየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል።