የትዊተር ተቀናቃኙ ትሪድስ ከኤለን መስኩ ትዊተር ምን የሚያመሳስል እና የሚለይ ነገር አለው?
ትሪድስ የአለማችን ቀዳሚው ቱጃር ኤለን መስክ በ44 ቢሊየን ዶላር የገዛውን ትዊተር መገዳደር ጀምሯል።
በአምስት ቀናት ውስጥ ከ100 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎችን ያፈራው የሜታው ትሪድስ በርካታ ነገሮቹ ከትዊተር ጋር ይመሳሰላሉ ቢባልም ልዩ የሚያደርጉት ነገሮችም አሉ።
ኢንስታግራም ጋር የተሳሰረው ትሪድስ 500 ቃላት እና ምልክቶችን በመጠቀም መልዕክት መለጠፍ ያስችላል።
በመተግበሪያው 5 ደቂቃ ርዝማኔ ያላቸውን ቪዲዮዎች መለጠፍ እንደሚቻልም ተነግሯል።
ከ353 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚ ያለው ትዊተር በበኩሉ በሃሽታግ፣ የቀጥታ መልዕክት መላክ በማስቻልና መነጋገሪያ የሆኑ ጉዳዮችን በመጠቆም ከትሪድስ ይለያል ተብሏል።
የትሪድስ እና ትዊተር አንድነት እና ልዩነትን ይመልከቱ፦