የዓለም ዋንጫዋ ጀግና ከድል በኋላ አስደንጋጭ ዜና አጋጠማት
ፌደሬሽኑ የካርሞና አባት የጠና ህመም እንደነበረባቸው እና አርብ እለት ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል
የሰፔን ቡድን አምበል እና የዓለም ዋንጫ ጨዋታ የፍጻሜ ውድድር ጀግና ኦልጋ ካርሞና ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ የአባቷን ሞት ዜና መስማቷን የስፔን እግርኳስ ፌደሬሽን ገልጿል
በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ጀግና የተባለችው ኦልጋ ካርሞና ከፍጻሜ ውድድር ድል በኋላ አስደንጋጭ ዜና ሰምታለች።
የሰፔን ቡድን አምበል እና የዓለም ዋንጫ ጨዋታ የፍጻሜ ውድድር ጀግና ኦልጋ ካርሞና ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ የአባቷን ሞት ዜና መስማቷን የስፔን እግርኳስ ፌደሬሽን ገልጿል።
ካርሞና ስፔን የመጀመሪያዋ የሆነውን የሴቶች የዓለም ዋንጫ እንግሊዝን 1 ለ 0 በማሸነፍ እንድታነሳ ያስቻላትን ጎል ጨዋታው በተጀመረ በ29ኛው ደቂቃ አስቆጥራለች።
"እግር ኳስ ፌጀሬሽኑ የኦልጋ ካርሞናን አባት ህይወት ማለፍ ሲያሳወቅ በጥልቅ ሀዘን ውስጥ ሆኖ ነው። ተጨዋቿ አሳዛኙን ዜና የሰማችው የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ" መሆኑን የስፔን እግር ኳስ ፌደሬሽን ገልጿል።
"በጥልቅ ሀዘን ውስጥ ላሉት ኦልጋ እና ቤተሰቦቿ መጽናናትን እንመኛለን። አልጋ እንቺ የስፔን እግር ኳስ ታራክ ነሽ" ብሏል ፌደሬሽኑ።
ፌደሬሽኑ የካርሞና አባት የጠና ህመም እንደነበረባቸው እና አርብ እለት ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል።
እንደ ስፔኑ ሬልቮ ሚዲያ የካርምና ቤተሰቦች እና ጎደኞቿ የአባቷን ህይወት ማለፍ አለመናገራቸውን እና በህይወቷ ትልቅ በተባለው ውድድር ላይ እንድታተኩር አድርገዋል።
የካርሞና እናት እና ወንድሞች የዓለም ዋንጫውን ለማየት ኒውዝላንድ ሄደው የነበረ ቢሆንም በፍጥነት ወደ ሰፔን ተመልሰዋል።