በሚቀጥለው የፈረንጆቹ 2023 የሚጠበቁ አምስት ምርጫዎች
ሀ ብሎ ለመጀመር የሰዓታት እድሜ የቀሩት 2023 ዓመት ሁለት የአፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ አምስት ተጠባቂ ምርጫዎችን ያስተናግዳል።
በፈረንጆቹ 2023 በዓለም ዙሪያ ሚሊዮኖች ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በሚቀጥለው የፈረንጆቹ 2023 የሚጠበቁ አምስት ምርጫዎች
በፈረንጆቹ 2023 በዓለም ዙሪያ ሚሊዮኖች ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በዲሞክራሲ በርካታ ሀገራት በምርጫ ካርዳቸው ይበጀኛል ያሉትን መንግስት ሲመርጡ፤ እንደ የዋጋ ግሽበት እና ሙስና ያሉ የጋራ አበይት ጉዳዮችን ይጋራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዘ ኮንቨርሴሽን ባጠናከረው ዘገባው በ2023 ቁልፍ የሆኑ ብሄራዊ ምርጫዎች ምን አይነት መልክ ይኖራቸዋል የሚለው ከወዲሁ እየተጠበቀ ነው።
ናይጄሪያ (የካቲት)
የናይጄሪያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፖለቲካውን እንደሚመስል ጥርጥር የለውም እየተባለ ነው። የሀገሪቱ ፖለቲካ ከመልካኣ-ምድራዊና ኃይማኖታዊ ልዩነት ጋር በጥልቅ የተሳሰረ ነው። በሙስሊም ሰሜን እና በክርስቲያኑ ደቡብ መካከል ጥብቅ ፉክክር እንደሚኖር ታምኗል።
ለስምንት ዓመታት የሰሜን ተወላጅ የሆኑት ሙሃማዱ ቡሃሪ የፕሬዝዳንትነት ስልጣንን ከያዙ በኋላ ክርክሩ ስልጣኑ ወደ ደቡብ "መቀየር" አለበት በሚለው ላይ እንደሚያተኩር ተንታኞች ተናግረዋል።
ቡሃሪ በህገ መንግስቱ መሰረት ለሁለት የስልጣን ዘመን ካገለገሉ በኋላ ስልጣናቸውን ይለቃሉ። ይህ ደግሞ የምርጫውን ሁኔታ ይለውጠዋል ነው የተባለው።
ቱርክ (ሰኔ)
ዘ ኮንቨርሴሽን ቱርካዊያን እያንዳንዱን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ታሪካዊ ብለው ይጠሩታል ብሏል። ነገር ግን የሰኔ 2023 ምርጫ የእውነት ታሪካዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ምርጫው እየጠነከረ የመጣው የፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አገዛዝ የሀገሪቱን ፖለቲካ መቆጣጠሩን ወይም አለመቆጣጠሩን ይወስናል።
ከወዲሁ እጩዎችን የማፈንና የማሰር ተግባር መፈጸም ምርጫው ከጀርባው ምን እንዳዘለ መገመትን ቀላል አድርጎታል። አደጋው የቱርክ ተቃዋሚዎች የወደፊት ተስፋቸው እንዲሟጠጥ ያደርጋልም ተብሏል።
ዚምባቡዌ (ከሀምሌ እስከ ነሀሴ ባለው ጊዜ)
የፈረንጆቹ 2023 የዚምባብዌ ምርጫ የሀገሪቱ የቀድሞ መሪ ሮበርት ሙጋቤ ከወደቁ በኋላ የሚካሄድ ሁለተኛው ብሄራዊ ምርጫ ይሆናል።
የሀገሪቱ የመጨረሻ ምርጫ በወታደራዊ መፈንቅለ-መንግስት የሮበርት ሙጋቤ የ37 ዓመታት አገዛዝ ከተቋጨ ከአንድ አመት በኋላ በ2018 ነበር የተካሄደው። ሆኖም የአያሌ የዚምባብዌ እና የውጭ መንግስታት ተስፋን በተቃራኒ ያደረገ ምርጫ ከሰፊ አጨቃጫቂ እና የአመጽ ምርጫ በሚል በታሪክ ትልቅ ስፍራ ይዟል።
ዚምባብዌ በመጨረሻ ተቀባይነት ያለው ምርጫ ማካሄድ መቻሏ በ 2023 ቁልፍ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ነው ተብሏል። ምርጫው በተአማኒነቱ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ጉዳዮች አይን የተጣለበት ሆኗል። የምዕራባውያን መንግስታት እና እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ያሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከዓመታት የሻከረ ግንኙነት በኋላ ከዚምባብዌ ጋር ጠንካራ ምጣኔ-ሀብታዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመፍጠር እንከን የለሽ ብሄራዊ ድምጽ እንደ ቅድመ ሁኔታ ይፈልጋሉ ተብሏል።
አርጀንቲና (ጥቅምት)
የኳታሩ ዓለም ዋንጫን አሸናፊዋ አርጀንቲና ወደ 2023 የምርጫ ዓመት ስትገባ በፈተና ነው ተብሏል። የሀገሪቱ ምጣኔ-ሀብት ለረጅም ጊዜ ያሽቆለቆለ ሲሆን በላቲን አሜሪካ ከፍተኛ የነፍስ ወከፍ እዳ ያለባትም ሀገር ናት።
ሰማይ ላይ የደረሰ የዋጋ ግሽበት፣ ዝቅተኛ ደሞዝ እና ደካማ እድገት ተባብሰውባታል ተብሏል።
እነዚህ ሁሉ ችግሮች የፕሬዝዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ እና የኃያሉ ምክትላቸው ክሪስቲና ፈርናንዴዝ ደ ኪርችነር ቆይታ አጣብቂኝ ውስጥ አስገብቶታል ነው የተባለው።
ፓኪስታን (በ2023 መጨረሻ)
የፓኪስታን ምርጫ ተጠባቂ የሚያደርግባቸው ምክንያቶች አንዱ ከስልጣን የተባረሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን ፓኪስታንን ማስተዳደር የሚያስችላቸውን ሁለት ሶስተኛ አብላጫ ድምጽ ማግኘት ይችሉ? የሚለው ነው።
ምርጫው መቼ እንደሚካሄድ አለመታወቁ ትልቅ ጥያቄም አስነስቷል። በፓኪስታን አጠቃላይ ምርጫ በስልጣን ላይ ባለው መንግስት አይካሄድም። በምትኩ ጊዜያዊ መንግስት ተቋቁሞ ምርጫ በ90 ቀናት ውስጥ ያሰናዳል።