ዶናልድ ትራምፕ በ2024 ምርጫ ዳግም ለፕሬዝዳንትነት ሊወዳደሩ ነው
ትራምፕ እጩነታቸውን ሚያሳውቁት ፓርቲያቸው በአሜሪካ የላይኛውና የታችኛው ም/ቤት አብላጫ ወንበር ባጣ ማግስት ነው
ትራምፕ የፓርቲያቸው እጩነታቸውን እንዲያጸድቅ ይፈልጋሉ ተብሏል
ዶናልድ ትራምፕ የሪፐብሊካን ተፎካካሪዎችን ከውድድር ለማስወጣት ለዋይት ሀውስ እንደሚወዳደሩ ዛሬ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በርካታ ሪፐብሊካኖች በአጋማሽ ዘመን የምርጫ ውጤት ወቀሳ የደረሰባቸው የቀድሞው ፕሬዝዳንት፣ ዳግም ወደ ዋይት ሀውስ ለመምጣት እንደሚፈልጉ ከቀናት በፊት ጭላንጭል ሰጥተው ነበር።
ባልተለመደ ሁኔታ እጩነታቸውን ይፋ ያደርጋሉ የተባሉት ትራምፕ በፈረንጆቹ 2024 ምርጫ የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎችን ለመገርገር አስበው ሊሆን ይችላል እየተባለ ነው።
እነዚህ የፖርቲው ተፎካካሪዎቻቸው እውቅናቸው እየጨመረ የመጣውን የፍሎሪዳ ገዥ ሮን ዴሳንቲስ እና የትራምፕ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ናቸው።
ለ76 ዓመቱ ትራምፕ ቅርበት ያላቸው ምንጮች በዚህ አመት ባደረጉት ቅስቀሳ የተለያዩ ውጤቶች ቢኖሩም ወደፊት ለመግፋት ማቀዱን ገልጸዋል።
ትራምፕ ድጋፍ የሰጧቸው ሪፐብሊካኖች በአሜሪካ ሴኔት አብላጫ ድምጽ ባለማግኘታቸው በደጋፊዎቻቸው ዘንድ ድብልቅ ስሜት አለ ነው የተባለው። .
በአጋማሽ ዘመን ምርጫው በሰፊው “የምርጫ ማጭበርበር” ላይ ያተኮሩ አጀንዳዎችን ያራመዱና ከትራምፕ ጋር የተሰለፉ በርካታ እጩዎች ተሸንፈዋል።
ከምርጫው በፊት የተካሄደው የሮይተርስ ጥናት እንደሚያሳየው 53 በመቶ አሜሪካውያን እና ከአራት ሪፐብሊካኖች አንድ ለትራምፕ ጥሩ ምልከታ የላቸውም። በሕዝብ አስተያየቱ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው አሜሪካውያን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን በጥሩ ሁኔታ ተመልክቷቸዋል ተብሏል።
ትራምፕ የፓርቲያቸው እጩነታቸውን እንዲያጸድቅ ይፈልጋሉ ተብሏል። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ህጋዊ ውጣውረዶች ያሉባቸው ትራምፕ ከዋይት ሀውስ ሚስጥራዊ ሰነዶችን የማስወገድ የወንጀል ምርመራ እንዲሁም በካፒቶል ጥቃት በነበራቸው ሚና ጋር የተያያዘ ችግሮች አሉባቸው።
በደጋፊዎቹ ዘንድ ትራምፕ ያጋጠሟቸው የተለያዩ ምርመራዎች ፖለቲካዊ ምስል በመስጠት የወንጀል ጥርጣሬዎችን አይቀበሉም ሲል የዘገበው ሮይተርስ ነው።