ራይላ ኦዲንጋ በ2027 የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጡ
ፖለቲከኛው ራይላ ኦዲንጋ በ2022ቱ ምርጫ በዊሊያም ሩቶ መሸነፋቸው አይዘነጋም
ኦዲንጋ በ2027 በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚወዳደሩ ከሆነ ለስድስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው
ራይላ ኦዲንጋ በ2027 የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጡ።
በ2022ቱ የኬንያ ምርጫ የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ በ2027 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጡ፡፡
ራይላ ኦዲንጋ ከስትዝን ቲቪ ኬንያ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፤ ጊዜው ገና ቢሆንም በምርጫው የማይወዳደሩበት ምክንያት እንደሌለ ተናግረዋል፡፡
“አልወዳደርም ብየ አላስብም” ሊሉም ነው የተናገሩት ባለፉት አምስት ምርጫዎች ብርቱ ተፎካካሪ የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ፡፡
ይሁን እንጅ ኦዲንጋ በኬንያ የምርጫ ሂደት ላይ ቅሬታ እንዳላቸው አልሸሸጉም፡፡
በወርሃ ነሐሴ 2022 የተካሄደው ምርጫና ያስከተለው ውዝግብ እጅግ እንደሚያሳስባቸው የገለጹት አንጋፋው ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ፤ “ኬንያውያን የሰጡት ድምጽ የማይቆጠርላቸው ከሆነ ለምን ድምጽ ይሰጣሉ ?” ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
ኦዲንጋ በ2027 በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚወዳደሩ ከሆነ ለስድስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡
በነሃሴ ወር 2022 በተካሄደው የኬንያ ፕሬዝዳታዊ ምርጫ ዶ/ር ዊያልየም ሩቶ ተቀናቃኛቸው ራይላ ኦዲንጋን በማሸነፍ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው የሚታወስ ነው፡፡
ዊሊያም ሩቶ ተቀናቃኛቸውን ራይላ ኦዲንጋን በ50 ነጥብ 49 በመቶ በሆነ ድምጽ ማሸነፋቸውም ነበር የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን በወቅቱ ይፋ ያደረገው፡፡
በሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተረጋገጠው የመጨረሻ ብይንም ይህንኑ ነበር፡፡
ዴምክራሲያዊ እንደነበር በኢጋድ እና በአፍሪካ ህብረት በተመሰከረለት ምርጫ 22 ሚሊዮን ኬንያውያን መሳተፋቸውም አይዘነጋም፡፡