ያላገቡ ዜጎች የሚበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ኖርዌይ እድሜያቸው ለጋብቻ ከደረሱ ጠቅላላ ህዝቧ ውስጥ 46 በመቶው ያላገቡ ናቸው
የአውሮፓ ሀገራት ከሌሎች አህጉራት ጋር ሲነጻጸሩ ዝቅተኛ የተጋቢዎች ቁጥር ያለበት ተብሏል
ያላገቡ ዜጎች የሚበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
የዓለማችን ሀብታሙ አህጉር የሚባለው አውሮፓ ዝቅተኛ ጋብቻ የሚፈጸምበት ሲሆን የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራ ደግሞ ከፍተኛ ጋብቻ የሚፈጸምበት አካባቢ ነው፡፡
እንደ ዓለም አቀፉ የስነ ህዝብ ጥናት ተቋም ሪፖርት ከሆነ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ስዊድን እና ጀርመን ዝቅተኛ የተጋቢዎች ቁጥር ያለባቸው ሀገራት ናቸው፡፡
እድሜያቸው ለጋብቻ ከደረሱ ዜጎቻቸው ውስጥ በኖርዌይ 46 በመቶ፣ በዴንማርክ 44 በመቶ፣ ፊንላንድ 43 በመቶ ፣ስዊድን 42 በመቶ እንዲሁም ጀርመን ደግሞ 40 በመቶ ያህሉ ላጤዎች ናቸው ተብሏል፡፡
ከዓለም ጠቅላላ ህዝብ 8 ቢሊዮን ያህል ውስጥ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ያህሉ ያላገባ ሲሆን እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ከሆኑት ውስጥ ደግሞ 47 በመቶ ያህሉ ያገቡ እንደሆኑ የተቋሙ ሪፖርት ያስረዳል፡፡
ያላገቡ ዜጎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ የመጣ ሲሆን የኑሮ ውድነት፣ ግለኝነት፣ ሀላፊነት የመውሰድ ፍላጎት ማጣት እና የፖለቲካ አለመረጋጋቶች የሚያገቡ ዜጎች ቁጥር እንዲቀንስ ያደረጉ ዋነኛ ምክንያቶች እንደሆኑ ይገለጻል፡፡