ጠንካራ ፓስፖርት ያላቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
አረብ ኢምሬት፣ ስፔን እና ፊንላንድ ጠንካራ ፓስፖርት ካላቸው ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
84ኛ ደረጃ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወደ 14 ሀገራት ያለ ቪዛ የሚያስኬድ ሲሆን 141 ሀገራት ደግሞ ቪዛ እንዲኖር ያስገድዳሉ
ጠንካራ ፓስፖርት ያላቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
በየዓመቱ የሀገራትን ፓስፖርት ጥንካሬ ይፋ የሚያደርገው ፓስፖርት ኢንዴክስ የተሰኘው ድረገጽ የ2024 ደረጃን ፋ አድርጓል፡፡
በዚህ ሪፖርት መሰረት የአረብ ኢምሬት ፓስፖርት ያለ ቪዛ ወደ 133 ሀገራት መጓዝ የሚቻል ሲሆን ቪዛ ግዴታ የሆነባቸው ሀገራት ደግሞ 18 ብቻ ናቸው፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የስፔን ፓስፖርት ሲሆን ይህም 134 ሀገራት ያለ ቪዛ መጓዝ ሲያስችል በ19 ሀገራት ላይ ደግሞ የግዴታ ቪዛን ይጠይቃል፡፡
ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን ከሶስተኛ እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ የያዙ ሀገራት ሲሆኑ ሶሪያ፣አፍጋኒስታን እና ኢራቅ ደግሞ የመጨረሻዎቹን ደረጃ የያዙ ሀገራት ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ፓስፖርት በ84ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን 16 ሀገራትን በልጦ ወደ 14 ሀገራት ያለ ቪዛ መጓዝ ያስችላል፡፡
43 ሀገራት የኢትዮጵያን ፓስፖርት ለያዙ ሀገራት ድንበራቸው ላይ ቪዛ ይሰጣሉ የተባለ ሲሆን 141 ሀገራት ደግሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ላለው ሰው ወደ ሀገራቸው የሚገባው ቪዛ ካለው ብቻ ነው ሲሉ ግዴታ ጥለዋል፡፡
ከአፍሪካ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን የመጨረሻዎቹን ደረጃ ከያዙ ሀገራት መካከል ናቸው፡፡