30 በመቶውን መሬትና ውቅያኖስ የሚጠብቀው አዲሱ ዓለም አቀፍ ፈንድ
ፈንዱ ክፉኛ የተፈጥሮ አደጋ እየደረሰባቸው ያሉ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራቱ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነው
በቫንኩቨር ካናዳ የተካሄደው ሰባተኛው የአካባቢ አስተባባሪ ም/ቤት ጉባኤ፤ የ185 ሀገራት 'ጥብቅ ፈንድ' ለመመስረት ተስማምተዋል
ዓለም አቀፉ የአካባቢ አስተባባሪ በ2030፤ 30 በመቶውን መሬትና ውቅያኖስ ለመጠበቅ ዓለም አቀፍ ፈንድ ይፋ አድርጓል።
ፈንዱ ክፉኛ የተፈጥሮ አደጋ እየደረሰባቸው ያሉ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራቱ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነው።
ጾታን ባማከለ ሁኔታና ከሀገሬው ነባር ሰዎች ጋር በትብብር ይሰራል።
ብዝሀ ህይወትን ለመጠበቅ በተቀመጠው መዋቅር መሠረት የሚተገበር ይሆናል።
በቫንኩቨር ካናዳ የተካሄደው ሰባተኛው የአካባቢ አስተባባሪ ም/ቤት ጉባኤ፤ የ185 ሀገራት 'ጥብቅ ፈንድ' ለመመስረት ተስማምተዋል።
ካናዳ ለዚህ ፈንድ 200 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም እንግሊዝ 100 ሚሊዮን ፓውንድ ለመለገስ በዚሁ ጉባኤ ቃል ገብተዋል።
በሰደድ እሳቶች ብዝሀ ህይወትንና የዱር አራዊቶች ህይወት አደጋ ላይ በመውደቁ ለመጠበቅ መዋዕለ ነዋይ ማሰባሰብና መመደብ ላይ አተኩሯል።
ጎርፍ፣ ከባድ የአየር ጸባይ እንዲሁም የሰው ልጅ እንቅስቃሴዎች አደጋ ደቅነዋል። የመንግስቱ ድርጅት በ2030፤ 30 በመቶውን መሬትና ውቅያኖስ ለመጠበቅ ድጋፍን ሽቷል።
ገንዘቡን ከሀገራት፣ ከለጋሽ ግለሰቦችና ከግሉ ዘረፍ ለመሰብሰብ እቅድ ተይዟል።