የዓለም ብዝሀ ህይወት ፈንድ ከሁለት ዓመት በኋላ ስራ እንደሚጀምር ይጠበቃል
ሀገራት እና ተቋማት ለብዝሀ ህይወት ፈንድ በዓመት እስከ 20 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያዋጡ ይጠበቃል
ሀገራት እና ተቋማት ለብዝ ህይወት እንዲያዋጡ የሚያስገድደው ህግ ከጥቂት ወራት በኋላ እንደሚጸድቅ ተገልጿል
የዓለም ብዝሀ ህይወት ፈንድ ከሁለት ዓመት በኋላ ስራ እንደሚጀምር ይጠበቃል።
ዓለማችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በአየር ንብረት ለውጥ እየተፈተነች ሲሆን የያዝነው ዓመት ከፍተኛ ሙቀት የተመዘገበበት ዓመት ሆኖ አልፏል።
የመንግስታቱ ድርጅት በየዓመቱ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ እያካሄደ ሲሆን የተባበሩት አረብ ኢምሬት የዘንድሮውን ጉባኤ ታዘጋጃለች።
በዱባይ በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ የዓለም ሀገራት መሪዎች፣ የአየር ንብረት እና አካባቢ ጥበቃ ምሁራን እና ተሟጋቾች እንደሚገኙም ይጠበቃል።
በዚህ ጉባኤ ላይ በጉጉት ከሚጠበቁት ውሳኔዎች መካከል በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተጎዱ ሀገራት የደረሰባቸውን የጉዳት መጠን መመዝገብ እና ካሳ እንዲያገኙ የሚያስገድደው ፖሊሲ አንዱ ነው።
ይህ ፖሊሲ የሚተገበርበት የቴክኒክ አሰራሮች እንደሚጸድቁ የሚጠበቅ ሲሆን በተለይም የበለጸጉ ሃገራት ከአምራች ኢንዱስትሪዎቻቸው በሚለቀቁ በካይ ጋዝ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ታዳጊ ሀገራት ካሳ እንዲከፍሉ የሚጠይቀው ህግ ዋነኛው ነው።
የዓለም ብዝሀ ህይወት ፈንድ ስራ አስፈጻሚ ካርሎስ ሮድርጊዩዝ ለአልዐይን እንዳሉት ለምድራችን የሚዋጣው ገንዘብ እጅግ ጠቃሚው ሀብት እንደሆነ ተናግረዋል።
የዓለም ሀገራት እና ተቋማት ከፈረንጆቹ 2025 ጀምሮ ለብዝሀ ህይወት ፈንድ በዓመት እስከ 20 ቢሊዮን ዶላር ያዋጣሉ ተብሎ ይጠበቃልም ብለዋል።