ይህ አነጋጋሪ የእግር ኳስ ውድድር የዓለማችን ብዙ ጎሎች የተቆጠሩበት እና ለረጅም ሰዓት የተካሄደ በሚል ተመዝግቧል
825 ጎሎች የተቆጠሩበት አነጋጋሪው የአግር ኳስ ውድድር
በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው እግር ኳስ ከስፖርት ውስጥ አንዱ ነው፡፡
ከፍተኛ በጀት እና የሰው ሀይል የሚሳተፍበት እግር ኳስ ውበቱን እና ተወዳጅነቱን ለመጨመር ፊፋን ጨምሮ በርካታ ሀገራት እና ሌሎች ተቋማት በየጊዜው አዳዲስ ህጎችን እያወጡ ናቸው፡፡
ከሰሞኑ በሩሲያ የሆነው ግን አግር ኳስ እንዲህም ነው እንዴ አስብሏል፡፡
ውድድሩ በሩሲያ መዲና ሞስኮ ከተማ አቅራቢያ ባለው ሉዝኒኪ ኦሎምፒክ ስፖርት ማዕከል ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
ነጭ እና ቀይ ቡድን በሚል ቡድኖች መካከል የተካሄደው ይህ የእግር ኳስ ውድድር ለ26 ሰዓታት ሳይቋረጥ ተካሂዷል፡፡
ባየር ሙኒክ ሮታች ኢገርን የተባለ እግር ኳስ ክለብን 27ለ0 በሆነ ውጤት አሸነፈ
በዚህ ውድድር ላይ ቀይ ቡድን ነጮችን 416 ለ409 ጎል ያሸነፈ ሲሆን በአጠቃላይ በውድድሩ 825 ጎሎች ተቆጥሮበታል፡፡
ይህ አነጋጋሪ የእግር ኳስ ውድድር ተጫዋቾች በየ ሁለት ሰዓቱ የስምንት ደቂቃ እረፍት ሲያደርጉ ነበር ተብሏል፡፡
ሰባት ሰባት ተጫዋቾች የተሳተፉበት ይህ እግር ኳስ ውድድር ዓላማው ለረጅም ሰዓት የተካሄደ እና ብዙ ጎሎች የተቆጠሩበት እግር ኳስ ውድድር በሚል አዲስ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ለመመዝገብ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ከዚህ በፊት በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ለረጅም ሰዓታት በሚል ተመዝግቦ የነበረው በፈረንጆቹ 2014 ላይ ሲሆን ለ24 ሰዓታት ተጫውተዋል፡፡