ዱባይ እና አቡዳቢ ደግሞ የነዚህ ቢሊየነሮች ዋነኛ ምርጫዎች መሆናቸው ተገልጿል
የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የዓለም ባለጸጋዎችን በመሳብ ቀዳሚ ሀገር ሆነች፡፡
ዓለም አቀፉ የቢዝነስ መረጃዎች ድርጅት የሆነው ፎርብስ እንዳለው ከሆነ የተባበሩት አረብ ኢምሬት በአረቡ ዓለም የመጀመሪያዋ የባለጸጋዎች መዳረሻ ሀገር ሆናለች፡፡
በዚህ ድርጅት የ2023 ሪፖርት መሰረትም በአረብ ኢምሬት 45 ቢሊየነሮች እና 134 ሺህ ሚሊየነሮች የሚኖሩባት ሀገር ተብላለች፡፡
በየዓመቱ ወደ አረብ ኢምሬት ከተሞች የሚፈልሱ ባለጸጋዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን በ2022 ዓመት ብቻ የ18 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
የዓለም ባለጸጋዎችን በመሳብ ከዓለም 11ኛ ሀገር የሆነችው አረብ ኢምሬት አቡዳቢ እና ዱባይ ደግሞ በነዚህ ባለጸጋዎች ለመኖሪያነት የተመረጡ ከተሞች ናቸው፡፡
የናጠጡ ሀብታሞች ማለት 30 ሚሊዮን ዶላር እና ከዛ በላይ ሀብት ያላቸው ሲሆኑ የተሻለ ምቾት እና ሀብት ፍለጋ መኖሪያቸውን በየጊዜው በመቀያየር የሚታወቁም ናቸው፡፡
በዓለማችን ሀብታቸው 30 ሚሊዮን ዶላር እና ከዛ በላይ የሖኑ ባለጸጋዎች ቁጥር 579 ሺህ 625 ሲሆኑ ሀብታቸው ባሳለፍነው ዓመት የ3 ነጥብ 8 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡
አሜሪካ የአለማችን ባለጸጋዎች ሀገር ስትሆን የዓለምን 42 በመቶ ገደማ ሀብት እንደያዙ ተገልጿል፡፡