ድርጅቱ እያንዳንዳቸው ቢበዛ የአምስት ዶላር ዋጋ ያላቸው 120 ሚሊዮን ክትባቶች ልሰጥ ነው አለ
ድርጅቱ እያንዳንዳቸው ቢበዛ የአምስት ዶላር ዋጋ ያላቸው 120 ሚሊዮን ክትባቶች ልሰጥ ነው አለ
የዓለም ጤና ድርጅት በትናንትናው እለት እንዳስታወቀው በድህነት ውስጥ ላሉ ሀገራት እያንዳንዳቸው ቢበዛ አምስት ዶላር ዋጋ ያላቸው 120 ሚሊዮን የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች እንደሚያካሂድ ገለጸ፡፡
የድርጅቱ ኃላፊ ቴድሮስ አድሃኖም፤ የክትባት አምራቹ አቦት ኤብቲኤንና ኤስዲ ባዮሴንሰር ከቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ በቀላሉ ሊሰጡ የሚችሉ 120 ሚሊዮን ክትባቶችን ለመስጠት ተስማምተዋል፡፡
ኃላፊው እንደተናገሩት የአንድ ክትባት ዋጋ አምስት ዶላር ሲሆን ከዚህ ባነሰ ዋጋ እንደሚቀንስ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
“ይህ የምርመራውን ስፋት በተለይም የምርመራ ቁሳቁስና የሰለጠነ የሰው ሃይል በሌለባቸው አካባቢዎች የሚጨምር ” መሆኑን ዶ/ር ቴድሮስ ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው ይህ የከፍተኛ የስርጭት መጠን ባለባቸው አካባቢ ያለውን የምርመራ አቅም የሚያሳድግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ታህሳስ ወር በቻይና ሁቤ ግዛት የተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ በመላው ዓለም ተዛምቶ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ አስከትሏል፡፡