ጉቴሬዝ ከ‘ኦሚክሮን’ጋር በተያያዘ የተጣሉ የጉዞ እገዳዎችን ‘አፓርታይድ’ ሲሉ ኮነኑ
የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ብቸኛው መንገድ ምርመራ እንደሆነም ገልጸዋል
ጉቴሬዝ እርምጃው ኢ-ፍትሐዊ ከመሆንም በላይ ውጤታማ እንደማይሆን ተናግረዋል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ‘ኦሚክሮን’ ከተባለው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ጋር በተያያዘ የተጣሉ የጉዞ እገዳዎችን “አፓርታይድ” ሲሉ ኮነኑ፡፡
ጉቴሬዝ በየትኛውም ሃገርም ሆነ ቀጣና ላይ የሚደረጉ እንዲህ ዐይነት የጉዞ ክልከላዎች ኢ-ፍትሐዊ ከመሆንም በላይ ውጤታማ እንደማይሆኑ ተናግረዋል፡፡
የተመድ ዋና ጸሃፊ በኢትዮጵያ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ
የጉዞም ሆነ ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴዎች ሳይስተጓጎሉ የወረርሽኙን ስርጭት መግቻ ብቸኛ መንገድ ምርመራ እንደሆነም ገልጸዋል ሌሎች የጥንቃቄ መንገዶችን መተግበሩ ሊዘነጋ የሚገባ እንዳልሆነ በመጠቆም፡፡
“ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለመጓጓዝ የሚያስችሉን ብዙ መንገዶች አሉን፤ ተቀባይነት የሌለውን እንዲህ ዐይነቱን ‘የጉዞ አፓርታይድ’ ለማቆም እነሱን እንጠቀም ነው የምለው” ሲሉም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ‘ኦሚክሮን’ ሲል የሰየመው አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በደቡብ አፍሪካ ተገኝቷል ተከትሎ ሃገራት በደቡብ አፍሪካ ቀጣና ባሉ ሃገራት ላይ የተለያዩ የጉዞ እገዳዎችን በመጣል ላይ ናቸው፡፡
እገዳው ተገቢ እንዳልሆነ የኮነኑ ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ አፍሪካ ሲዲሲን መሰል አህጉር አቀፍ ተቋማት እርምጃውን ተቃውመዋል፡፡
ከክትባቶች ፍትሐዊ ስርጭት ጉድለቶች ጋር በተያያዘ የመጣ እንደሆነ በማንሳት ድርጊቱን የሚኮንኑም ጥቂት አይደሉም፡፡ ጉቴሬዝም ይህን ነው ያሉት፡፡