ኦሚክሮን የተሰኘው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መዛመቱን ቀጥሏል
አሜሪካ እና የአውሮፓ አገራት ከደቡባዊ አፍሪካ አገራት በሚመጡ ተጓዦች ላይ ማዕቀብ በመጣል ላይ ናቸው
አዲሱ ቫይረስ እስካሁን ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በሰባት አገራት ላይ ተከስቷል
ኦሚክሮን የተሰኘው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መዛመቱን ቀጥሏል፡፡
የኮሮና ቫይረስ በቻይናዋ ዉሃን ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተከሰተ በኋላ በሁሉም የአለማችን አገራት ተከስቶ 261 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን አጥቅቶ ከ5 ነጥብ 1 በላይ ሚሊዮን ዜጎችን ደግሞ ገድሏል፡፡
በአውሮፓ እስከ የካቲት ድረስ 500 ሺህ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሊሞቱ ይችላሉ ተባለ
ይህ ቫይረስ ራሱን እየቀያረ ለተመራማሪዎች ፈተና በመሆን ብዙዎችን ያጠቃ ሲሆን አሁን ደግሞ ኦሚክሮን የተሰኘ አዲስ ዝርያ በደቡብ አፍሪካ ተገኝቷል፡፡
አዲሱ ዝርያ በደቡብ አፍሪካ መገኘቱን ተከትሎም አሜሪካ እና አውሮፓውያን የጉዞ እቀባ እና ሌሎች እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡
ይህ አዲስ ዝርያ ከደቡብ አፍሪካ ወደ ብዙ አገራት በመዛመት ላይ ሲሆን እስካሁን ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ ወደ ስድስት አገራት ተስፋፍቷል፡፡
ደቡብ አፍሪካ፣ እንግሊዝ፣ ቦትስዋና፣ ቻይና፣ ቤልጂየም እና እስራኤል እስካሁን አዲሱ ቫይረስ የተከሰተባቸው አገራት መሆናቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡
አውስትራሊያ፣አሜሪካ፣ ብራዚል፣ እንግሊዝ፣ ኢራን፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ሞሪሺየስ፣ ስሪላንካ፣ ፓኪስታን፣ ህንድ እና ሌሎችም አገራት ከደቡብ አፍሪካ ወደ አገራቸው በሚገቡ መንገደኞች ላይ እገዳ የጣሉ እና ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ የወሰኑ አገራት ናቸው፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ በደቡብ አፍሪካ እና አካባቢው አገራት ላይ እየተወሰደ ያለው የማግለል እርምጃዎች ትክክል አለመሆናቸውን ገልጾ እርምጃዎቹ የቫይረሱን ስርጭት አይገታውም ሲል አስጠንቅቋል፡፡
በኮሮና እስከ 180 ሺህ የሚደረሱ የጤና ባለሙያዎች ገድሏል- የዓለም ጤና ድርጅት
የእንግሊዝ መንግስት በበኩሉ ከደቡብ አፍሪካ እና ጎረቤቶቿ የሆኑት ቦትስዋና፣ ዚምባብዌ፣ ማላዊ፣ ኢስዋቲኒ፣ ሌሴቶ፣ ናሚቢያ፣ ሞዛምቢክ እና ዛምቢያ መንገደኞች ላይ የጉዞ እገዳ እና ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ወስኗል፡፡
የደቡብ አፍሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ኦሚክሮን የተሰኘው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በአገሯ መከሰቱን ተከትሎ ዓለም እያገለለን ነው እየተቀጣን ነው ሲሉ ድርጊቱን ኮንኗል፡፡