የኃያላኑ ሩሲያና ቻይና መሪዎች "አዲስ የዓለም ስርዓት" እንፈጥራለን አሉ
አዲሱ የዓለም፣ በዓለም አቀፍ መርሆችን እና ህጎችን ላይ ተመሰረተ ይሆናል ተብሏል
ፑቲን እና ሺ “ዓለምን በበላይነት ለመቆጣጠር የሚደረገው ሙከራ” አንቀበልም በሚል ጠንካራ አቋማቸው ይታወቃሉ
የምድራችን ኃያላኑ ሩሲያና ቻይና መሪዎች “አዲስ የዓለም ስርአት” እንፈጥራለን አሉ፡፡
መሪዎቹ ይህን ያሉት የቻይናው መሪ ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በሞስኮ በነበራቸው የሁለት ቀናት ጉብኝት በነበረው ዘለግ ያለ ውይይት ላይ ነው፡፡
ጉብኝቱ ትልቅ ትርጉም ያለውና የቻይናው መሪ ዓለም የእስር ማዘዣም ጭምር በማውጣት ጫና ለመፍጠር እየተረባረባበቸው ላሉት የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን ያላቸውን አጋርነት ያሳዩበት እንደሆነ እየተዘገበ ነው፡፡
የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር፣ ዓለምን በበላይነት ለመቆጣጠር አሜሪካ የምትደርገው እንደቅስቃሴ ማስቆም እንዲሁም ዩክሬን ጉዳይ መሪዎቹ በነበራቸው ቆይታ ከመከሩባቸው አንኳር ጉዳዮች ናቸው፡፡
"መሪዎቹይህ ግንኙነት ከሁለትዮሽ ያለፈና ለዓለም አቀፋዊ ገጽታ እና ለሰው ልጅ የወደፊት ህይወት ወሳኝ ጠቀሜታ እንዳለው መክረዋል" ስትል ባወጣቸው መግለጫ ገልጻለች፡፡
“ዓለምን በበላይነት ለመቆጣጠር የሚደረገው ሙከራ” አንቀበልም የሚል ጠንካራ የጋራ አቋም ያላቸው መሪዎቹ፤ በቀጣይ “አዲስ የዓለም ስርአት” እንፈጥራለንም ብለዋል፡፡
ፑቲን በበኩላቸው “የተባበሩት መንግስታት ዋና ሚና ፣ የጸጥታው ምክር ቤት፣ ዓለም አቀፍ ህግ እንዲሁም የተመድ ቻርተር አላማ እና መርሆች ላይ የተመሰረተ ይበልጥ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ የሆነ ሁሉን አቀፍ የዓለም ስርአት መፍጠር ላይ በትብብር እየሰራን ነው" ሲሉ መናገራቸው የክሬምሊን ድህረ-ገጽ አስነብቧል፡፡
ቻይና ፕሬዝዳንት ሺ “አሁን በ100 ዓመታት ውስጥ ያልተከሰቱ ለውጦች አሉ። አንድ ላይ ስንሆን እነዚህን ለውጦች እንመራለን” ሲሉ ለፑቲን መናገራቸውም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የቻይናው አቻቻው ሃሳብ የሚጋሩት ፑቲንም “እስማማለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ሺ መልሰው ፑቲንን “እባክህን ወዳጄ ራስህን ጠብቅ” ሲሉ ምን ያህል እንደሚጨነቁላቸው ነግረዋቸዋል፡፡
በትናንትናው አለት ቻይናው መሪ ፑቲንን አሞካሹ የሚሉ ዘገባወች ሲወጡ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይህ የቻይና እና ሩሲያ መሪዎች ወዳጅነት እንቅልፍ የነሳት አሜሪካም ታዲያ የቤጂንግ-ሞስኮ ግንኙነት የዩክሬን ጦርነትን የሚያበረታታ ነው ስትል ነቅፋለች፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቻይናው መሪ በሞስኮ በነበሩበት ወቅት የሩሲያ ጦር 21 ሻሄድ-136 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በዩክሬን ላይ “ግዙፍ የአየር ጥቃት” መሰንዘራቸውን የዩክሬን ጦር ሃይሎች ጄኔራል አስታውቋል።
ፕሬዝዳንተ ሺ ሞስኮን ለቀው ለመውጣት ሲዘጋጁም እንዲሁ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪቭ እና በዩክሬን ሰሜናዊ እና ምስራቅ አካባቢ መጠነ ሰፊ አየር ጥቃት ተፈጽሟል፡፡
ጥቃቱ በሩሲያ የሰው አልባ አውሮፕላኖች የተፈጸመው ሲሆን ስለደረሰው አስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡
እናም በርካቶች የሚያነሱት ጉዳይ ቢኖር የቻይነው መሪ ሞስኮ ቆይታ በዩክሬን ጦርነት ላይ የሚያመታው ለውጥ እንደሌለ ነው፡፡