ቻይና የጋራ ልምምዱ በሀገራቱ መካከል ያለው ትብብር በተግባር የተደገፈ መሆኑን ያረጋግጣል ብላለች
የቻይና የሩሲያ እና የኢራን የብህር ሃይሎች የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
የሶስቱ ሀገራት የብህር ሃይሎች በአይነቱ የተለየ ነው የተባለውን ወታደረዊ ልምምድ በኦማን ብሽረ ሰላጤ ላይ ማድረጋቸውም ነው የተነገረው።
ቻይና ለምምዱን አስመልክታ ባወጣችው መግለጫ፣ ከአሜሪካ ጋር የነገሰው ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ ልምምዱ በሀገራቱ መካከል ያለው ግንኙነት በተግባር የተደገፈ እንሆን ያስችላል ብላለች።
በተጨማሪም ልምምዱ በቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት ላይ አዎንታዊ ተጽእኖን እንደሚያሳድርም ነው የቻይና መከላለያ ሚኒስቴር ያስታወቀው።
በጋራ ወታደራዊ ልምምዱ ላይ ከኢራን እና ሩሲያ በተጨማሪ ሌሎችም ሀገራት እየተሳተፉ እንደሆነ የገለጸችው ቻይና እነማን እንደሆኑ ግን ዝርዝሩን ከመናገር ተቆጥባለች።
ቻይና በወታደራዊ ልምምዱ ላይ ሚሳዔል ታጣቂ የሆኑ "ናኒንግ" የተባሉ አውዳሚ የጦር መርከቦችን አሰመርታለች ተብሏል።
የሩሲያ፣ ቻይና እና ኢራን ወታደራዊ ልምምድ በትናትናው እለት ረቡእ ተተጀመረ ሲሆን እስከ ቀጣይ እሁድ ቀጥሎ እንደሚካሄድ ተነግሯል።