ዢ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪን በስልክ እንደሚያናግሩ ይጠበቃል
ሩሲያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂን ፒንግ የሞስኮ አቻቸውን ቭላድሚር ፑቲንን ማሞካሸታቸው ተሰምቷል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ተጨማሪ ውይይቶችን እንደሚያደርጉ እየተጠበቀ ነው።
የዢ ጉብኝት ለአንድ ዓመት የዘለቀውን ጦርነት የሚያበረታታ ነው በሚል በምዕራባውያን ነቀፌታ ገጥሞታል።
ሁለቱ መሪዎች ሰኞ ዕለት ከአራት ሰዓታት በላይ ተነጋግረዋል ተብሏል።
ቻይና በዩክሬን ግጭት ውስጥ ራሷን እንደ ሰላም ፈጣሪ ለማቅረብ ብትሞክርም፤ ጉብኝቱ በሞስኮ እና በቤጂንግ መካከል ያለውን መቀራረብ ያሳየ ነውም ተብሏል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ዋሽንግተን ቤጂንግን ለፑቲን "ዲፕሎማሲያዊ ሽፋን" ትሰጣለች ስትል ተወቅሳለች።
በአንጻሩ ዢ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪን በስልክ ብቻ ሊያናግሩ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ፑቲን እና ዢ ሰኞ እለት በክሬምሊን ሲገናኙ "ውድ ጓደኛዬ" በመባባል ሰላምታ መለዋወጣቸው ተነግሯል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን በቴሌቭዥን በተላለፈ አስተያየታቸው ቻይና የዩክሬን ግጭት ለመፍታት ያቀረበችውን ሀሳብ በአክብሮት መመልከታቸውን ለዢ ተናግረዋል።
ዢ በበኩላቸው ፑቲንን አወድሰው ሩሲያውያን በሚቀጥለው ዓመት በድጋሚ እንደሚመርጧቸው ተንብየዋል።