የቻይና ፕሬዝዳንት ዢ የሳዑዲና የአሜሪካ ግንኙነት ሻክሯል በተባለ ማግስት ሪያድን ሊጎበኙ ነው
ፕሬዝዳንት ዢ የሳዑዲ ጉብኝት የንግድ ግንኙነቶችን ማጠናከርና ክልላዊ ደኅንነት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ሳዑዲ ተናገረች
የቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ በታህሳስ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት ያደርጋሉ
የቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ በታህሳስ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሏል።
ፕሬዝዳንት ዢ በሚያደርጉት ጉብኝት የንግድ ግንኙነቶችን ማጠናከር እና ክልላዊ ደኅንነት ቅድሚያ እንደሚሰጥ የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አደል አል-ጁቤር አስታውቀዋል።
በታህሳስ ወር ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሁለት ምንጮች የገለጹ ሲሆን፤ ጉብኝቱ በሳዑዲ አረቢያ እና በአሜሪካ መካከል በነዳጅ አቅርቦት ላይ በተፈጠረው አለመግባባት እና በባህረ ሰላጤው ሀገራትና በቻይና መካከል እያደገ ያለው ትብብር ለአሜሪካ ስጋት ባለበት ወቅት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሚንስትር ዴኤታው ስለጉዞው ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም በቻይና እና በሳዑዲ መሪዎች መካከል የሚደረገው ጉብኝት "ተፈጥሯዊ" ነው ብለዋል።
አደል አል-ጁቤር በግብፅ ከተካሄደው የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ ጎን ለጎን ለሮይተርስ እንደተናገሩት ቻይና የሳዑዲ ዓረቢያ ትልቅየንግድ አጋር ናት ብለዋል። "በቻይና ከፍተኛ ኢንቨስትመንቶች አሉን፤ ቻይናውያንም በሳዑዲ አረቢያ ትልቅ ኢንቨስትመንቶች አሏቸው።
ጁቤር "በአደጋ ላይ ያሉ ግዙፍ አክሲዮኖች አሉን እና እነዚህ ጉብኝቶች ያልተለመዱ አይደሉም" ሲሉም አክለዋል። "ከሌሎች የንግድ አጋሮቻችን እና ስልታዊ አጋሮቻችን ጋር ተመሳሳይ ነው፤ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሀገራት የሚያደርጉት ይህንኑ ነው።" ብለዋል።