ዘሌንስኪ ከቤጂንግ የሰላም እቅድ በኋላ ከ ዢ ጂንፒንግ ጋር መገናኘት እፈልጋለሁ አሉ
ቻይና በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆም ባለ 12 ነጥብ የሰላም ሀሳብ ከሰሞኑን አቅርባለች
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቻይናን የሰላም እቅድ ውድቅ አድርገዋል
ዘሌንስኪ ከቤጂንግ የሰላም እቅድ በኋላ ከ ዢ ጂንፒንግ ጋር መገናኘት እፈልጋለሁ አሉ።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ከቻይና ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነትን ለማስቆም ባቀረቡት የሰላም ሀሳብ ላይ መወያየት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
ዘሌንስኪ የጦርነቱን የመጀመሪያ ዓመት አስመልክቶ ሲናገሩ ከቻይና ፕሬዝዳንት ጋር በመገናኘት በቤጂንግን የሰላም ሀሳቦች ዙሪያ ለመወያየት ማቀዳቸውን ተናግረዋል።
"ቻይና ለሩሲያ የጦር መሳሪያ እንደማትሰጥ ማመን እፈልጋለሁ" ሲሉም አክለዋል።
ቻይና በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆም ባለ 12 ነጥብ የሰላም ሀሳብ ከሰሞኑን አቅርባለች።
ቻይና የተኩስ አቁምና የሰላም ንግግር እንዲደረግ እንዲሁም ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ እንዲገቱ ጠይቃለች።
“በሀገራት በአንድ ወገን የሚጣሉ ማዕቀቦችን ማቆም አለባቸው” ያለችው ቤጂንግ፤ “የዩክሬንን ቀውስ ለማርገብ የድርሻቸውን ይወጡ” ስትልም ጥሪ አቅርባለ።
የሰላም እቅዱ “የቀዝቃዛው ጦርነት አስተሳሰብን” ያወግዛል ሲል ኢንዲፔንደንት ዘግቧል።
እስካሁን ድረስ ከቻይና ወገን ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ ላቀረቡት የውይይት ጥሪ ምላሽ አልተሰጠም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቻይናን የሰላም እቅድ ውድቅ አድርገዋል።
"እቅዱ ከሩሲያ ውጭ ማን እንደሚጠቀም የሚያሳይ አይደለም" ብለዋል።