የዛምቢያ ፕሬዝዳንትን ለመግደል ሲያሴሩ ነበር የተባሉት ጠንቋዮች
የሀገሪቱ ፖሊስ ጠንቋዮቹ እስስትን ጨምሮ ከሌሎች እቃዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል
ጠንቋዮቹ ፕሬዝዳንቱን ከገደሉ 73 ሺህ ዶላር እንደሚከፈላቸው ቃል ተገብቶልን ነበር ብለዋል
የዛምቢያ ፕሬዝዳንትን ለመግደል ሲያሴሩ ነበር የተባሉት ጠንቋዮች
በደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ዛምቢያ ጥንቆላ በሰፊው የሚታወቅ ሲሆን ከሰሞኑ የሐገሬው ዋነኛ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል፡፡
ነገሩ በይፋ መወራት የጀመረው ደግሞ የዘምቢያ ፖሊስ የሐገሪቱን ፕሬዝዳንት ሀካንዴ ሂቺለማን ለመግደል ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ጠንቋዮችን ይዣለሁ ማለቱን ተከትሎ ነው፡፡
ፖሊስ በመግለጫው ላይ እንደጠቀሰው በዛምቢያ ዋና ከተማ ሉሳካ ውስጥ ሁለት ጠንቋዮች ፕሬዝዳንቱን ለመግደል ሲንቀሳቀሱ ተይዘዋል ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ከሁለቱ ተጠርጣሪዎች ጋር በተለምዶ እስስት የተሰኘው ተሳቢ እንስሳን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶች እንደተያዙም ፖሊስ አክሏል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ሰጡት በተባለው ቃልም ፕሬዝዳንቱን ለመግደል 73 ሺህ ዶላር እንደሚከፈላቸው ከቀጣሪዎቻቸው ጋር ተስማተዋልም ተብሏል፡፡
አሜሪካ በጥንቆላ ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች
ኢማኑኤል ወይም ጃይ ጃይ ባንዳ የተሰኙት የዛምቢያ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ደግሞ ከዚህ ሁሉ የግድያ ሙከራ ጀርባ እጃቸው እንዳለበት ፖሊስ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡
በዛምቢያ ምክር ቤት ብቸኛው የግል ተወዳዳሪ ፓርላማ አባል የሆኑት እኝህ ፖለቲከኛ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኤድጋር ሉንጉ ወዳጅ ናቸው የተባለ ሲሆን በስልጣን ካሉት ፕሬዝዳንት ጋር አለመግባባት ውስጥ ናቸው፡፡
ጃይ ጃይ ባንዳ አሁን ላይ በእስር ላይ ሲሆኑ በስርቆት ወንጀል ተጠርጥረው ከሀገር ሊኮበልሉ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል፡፡
ዛምቢያን ጨምሮ በርካታ የደቡብ አፍሪካ ሀገራት ለጥንቁልና ከባድ ፍርሃት አለባቸው የተባለ ሲሆን በጥንቁልና የሚያምኑ ሰዎች ቁጥርም ቀላል እንዳልሆነ ተገልጿል፡፡