ጋና ጥንቆላ የሚያስከስስ ወንጀል መሆኑን የሚያስቀር ህግ ልታጸድቅ ትችላለች ተባለ
አፍሪካዊቷ ጋና ጥንቆላ በወንጀል የሚያስከስስ መሆኑን የሚያስቀር ህግ ልታጸድቅ ትችላለች ተብሏል
ጥንቆላ ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገራት በተለይም በገጠሩ ማህበረሰብ ያልተለመደ ነገር ባይሆንም ሴትዮዋ ተደብደበው የተገደሉበት መንገድ ከፍተኛ የህዝብ ቁጣ አስከትሏል
አፍሪካዊቷ ጋና ጥንቆላ በወንጀል የሚያስከስስ መሆኑን የሚያስቀር ህግ ልታጸድቅ ትችላለች ተብሏል።
ባለፈው አርብ እለት የጋና ፖርላማ በጥንቆላ የተከሰሱ ሰዎችን ለመከላከል የሚያስችል ረቂቅ ህግ አጽድቋል።
በሀገሪቱ በጥንቆላ የተሰማሩ ሰዎች ማህበሰሰባዊ መገለል እና ጥቃት ይደርስባቸዋል።
ይህ ረቂቅ ህግ የቀረበው በፈረንጆቹ 2020 በሳቫና ግዛት የ90 አመት አዛውንት ሴት በቡድን በመደብደባቸው እና ድርጊቱ በሀገሪቱ እና በአለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች በመወገዙ ምክንያት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ጥንቆላ ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገራት በተለይም በገጠሩ ማህበረሰብ ያልተለመደ ነገር ባይሆንም ሴትዮዋ ተደብደበው የተገደሉበት መንገድ ከፍተኛ የህዝብ ቁጣ አስከትሏል።
ረቂቅ አዋጁ በማህበረሱ የተገለሉ ጠንቋዮች የሚኖሩበት መጠለያም እንዲፈርስ ያዛል።
500 የሚሆኑ በዋናነት ህጻናት በእድሜ የገፉ ሴቶች በሀገሪቱ ሰሜናዊ ግዛት በእንዲህ አይነት አምስት መጠለያዎች እንደሚኖሩ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት አድርጎ ነበር።
"አዲሱ ህግ አጥፊዎች የሚከሰሱበትን... ተጎጅዎችን ወደ ማህበረሰቡ እና ወደ ቤተሰቦቻቸው የሚቀላቀሉበትን የህግ ማዕቀፍ ያዘጋጃል" ብለዋል በፖርላማው የህገመንግስት፣ የህግ እና የፖርላሜንታዊ ጉዳዮች ሊቀመንበር ክዋሜ አይማንዱ አንትቲዊ።
ህጉ ተግባራዊ እንዲሆን የጋናው ፕሬዝደንት ናኖ አኩፎ ማጽደቅ ይኖርባቸዋል።