ምዕራባውያን የሚረዱን ከሆነ "በእሳት" ውስጥም ሆነን ምርጫ ልናካሂድ እንችላለን- ዘለንስኪ
ፕሬዝደንቱ ይህን ያሉት የአሜሪካ ሴናተሮች ምርጫው በፈረንጆቹ 2024 የሚካሄድበትን ቀን እንዲያሳወቁ ላቀረbuላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ነው
አጋሮቻቸው ለምርጫው የሚያስፈገውን ወጭ የሚጋሯቸው ከሆነ ምርጫው ሊካሄድ እንደሚችል ዘለንስኪ ተናግረዋል
የዩክሬኑ ፕሬዘደንት ቮልድሚር ዘለንስኪ ምዕራባውያን እርዳታ የሚያደርጉ ከሆነ "እሳት" ውስጥ ሆነንም ቢሆን ምርጫው እናካሂዳለን አሉ።
ፕሬዝደንቱ ይህን ያሉት የአሜሪካ ሴናተሮች ምርጫው በፈረንጆቹ 2024 የሚካሄድበትን ቀን እንዲያሳወቁ ላቀረቡላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ነው።
አጋሮቻቸው ለምርጫው የሚያስፈገውን ወጭ የሚጋሯቸው ከሆነ ምርጫው ሊካሄድ እንደሚችል ዘለንስኪ ተናግረዋል።
በዩክሬን አሁን በየ90ቀናቱ በሚራዘመው ወታደራዊ ህግ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ የለም።
ኪቭን ነሐሴ 23 ከጎበኙት ከፍተኛ የአሜራካ ህግ አውጭዎች መካከል ሴናተር ሊንዲሴ ግርሃም ዪክሬን በሩሲያ ላይ የምታደርገውን መከላከል አድንቀዋል፤ ነገርግን በጦርነት ውስጥ ሆና ምርጫ ማካሄድ እንደምትችል ማሳየት አለባት ብለዋል።
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ 1+1 ከተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቆይታ በገንዘብ ድጋፍ እና ህግን መቀየር ጉዳይ ከግርሃም ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዝደንቱ ለግርሃም በሰጧቸው ቀላል እና ፈጣን መልስ ግርሃም ደስተኛ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።
ዘለንስኪ የምርጫ ታዛቢዎች ምሽግ ድረስ መሄድ እንዳለባቸው እና በውጭ ለሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የመምረጥ እድል ሊመቻችላቸው ይገባል ብለዋል።