ዚምባብዌ በሰብአዊ መብት ጥሰት ምክንያት በአውሮፓና በአሜሪካ ማእቀቦች ስር ነች
ዚምባብዌ ልማትን እያደናቀፈ እና ለኢኮኖሚ ውድቀት ምክንያት የሆነውን ማዕቀብ እንዲነሳላት ለአውሮፓ ህብረት እያመለከተች ነው ፡፡
ዚምባብዌ ጥያቄውን ያቀረበችው የአውሮፓ ህብረትና ዚምባብዌ በትናንትናው እለት በዝግ ከተወያዩ በኋላ ነው፡፡
የዚምባብዌ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፍሬድሪክ ሻቫ ከዝግ ስብሰባው በኋላ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት በሀራሬ እና በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነቶች እና የንግድ ግንኙነቶች ያለገደብ እንዲቀጥልና የአውሮፓ ህብረት ማዕቀቡን እንዲያስወግድ መወያየታቸውን ተናግረዋል ፡፡
ሟች የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ በሀገሪቱ የሕግ የበላይነትን እና የሰብአዊ መብቶችን አለማክበራቸውን ተከትሎ ዚምባብዌ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ህብረት ማዕቀቦች ስር ወድቃ ቆይታለች፡፡ አዲሱ ዘመን ሲመጣ እንኳን ሁኔታው አልተለወጠም ብለዋል ሚኒስትር ሻቫ ፡፡ “ዚምባብዌ የአውሮፓ ህብረት ማዕቀቦችን ማደሱን መቀጠሉን በጸጸት ተናግራች ፡፡”
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በውይይታቸው መልእክቱ በግልጽ ወደ አውሮፓ ህብረት እንዲደርስና ማዕቀቦች እንዲወገዱ ጠይቀዋል፡፡
ሻቫ ሀገሪቱ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በጥሩ ገጽታዎች ተመልሳ እንደምትመጣ ለማረጋገጥ ፈቃደኛ መሆኗን እና ተጨማሪ ተሳትፎዎችን በጉጉት እንየጠበቀች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“ከሁሉም በላይ ደግሞ ዚምባብዌ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያለን ግንኙነት እስከሚመለከተው ድረስ እንደገና ለመሳተፍ ጥረቷን አጠናክራለች ፡፡” በዚምባብዌ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ቲሞ ኦልኮነን እንደተናገሩት ውይይቱ ለሁለቱም ወገኖች በሁሉም ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ እድል እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል ፡፡
“የዴሞክራሲ ምህዳሩ እየጠበበ መምጣቱን ፣ በፀጥታ ኃይሎች የሚፈጸሙትን ሁሉንም ዓይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለመፍታት መሻሻል አለመኖሩ፣ በግዳጅ የተሰወሩ ጉዳዮችን በጥልቀት የመመርመር ችግር አለብን ፡፡
የህብረቱ አምባሳደር ህብረቱ ከሀገሪቱ ጋር በንግድና ከሮና ቫይረስን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት እንደግፋለን ብለዋል፡፡