ሱዳንና አሜሪካውያን የ“ዩኤስኤስ ኮል”ተጎጅ ቤተሰቦች ሱዳንን ከሽብር ዝርዝር ለመሰረዝ መንገድ የሚከፍት ስምምነት ላይ ደረሱ
ሱዳንና አሜሪካውያን የ“ዩኤስኤስ ኮል”ተጎጅ ቤተሰቦች ሱዳንን ከሽብር ዝርዝር ለመሰረዝ መንገድ የሚከፍት ስምምነት ላይ ደረሱ
የሱዳን የሽግግር መንግስትና አልቃኢዳ በ“ዩኤስኤስ ኮል” ላይ ባካሄደው የቦንብ ድብደባ ጉዳት የደረሰባቸው አሜሪካውያን የቤተሰብ አባለት፣ ሱዳን “ሽብርን ከሚደግፉ መንግስታት ዝርዝር” ውስጥ የምትሰረዝበትን መንገድ የሚያመቻች ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ አገኘሁት እንዳለው መግለጫ ከሆነ የፍትህ ሚኒስትሩ ናስር አል ዲን አብደል ባሪ ካርቱም እ.ኤ.አ. በ2000 በአልቃኢዳ የቦንብ ድብደባ ለተገደሉት 17 መርከበኞች ቤተሰቦች 30 ሚሊዮን ዶላር እንደምትከፍል ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡
አብድል ባሪ የተደረገው ስምምነት፣ ሱዳን ለክስተቱ ምንም ኃላፊነት እንደሌለባት በግልጽ የሚያስቀምጥ ብለዋል፡፡
የሱዳን መንግስት እንዲህ አይነት ስምምነት ውስጥ የገባው በቀድሞው አገዛዝ ምክንያት ሀገሪቱ ከገባችበት ታሪካዊ ጥርጣሬ ላማስወጣትና፣ የአሜሪካ መንግሰት ሱዳን ሽብርን ከሚደግፉ መንግስታት ዝርዝር ውስጥ እንትወጣ እንደቅደም ሁኔታ በማስቀመጡ ነው ብለዋል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2014 የአሜሪካ ፍርድቤት አልቃኢዳ በሱዳን በመደገፍ 17 አሜሪካውያን እንዲገደሉ አድርጋለች ብሎ ነበር፤ ስለሆነም የአሁኑ ስምምነት ጉዳዩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመዝጋት ነው ብለዋል፡፡
ባለፈው ጥር ወር መጨረሻ አብደል ባሪ ከአሜሪካ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናጂይ ጋር መገናኘታቸው ሱዳን ከአሜሪካ ጋር ያላትን ጥረት የሚየሳይ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ቲቦር ናጂይ የሽብር ሰለባዎች ካሳ ለአሜሪካ መንግስት ቀዳሚ አጀንዳ ነው ብለዋል፡፡