የዚምባብዌ ጤና ሚኒስትር የ60 ሚሊዮን ዶላር ግምት ባለው የኮቪድ 19 መሳሪያ ውል ምክንያት ታሰሩ
የዚምባብዌ ጤና ሚኒስትር የ60 ሚሊዮን ዶላር ግምት ባለው የኮቪድ 19 መሳሪያ ውል ምክንያት ታሰሩ
የዚምባብዌ ጤና ሚኒስትር ኦማዲህ ሞዮ የ60 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ባላቸው የኮቪድ 19 መሳሪያዎች ግዥ ላይ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው በፖሊስ መያዛቸው ተነግሯል፡፡
የጤና ሚኒስትሩን መያዝ የዚምባብዌን ሚዲያዎች ጠቅሶ የዘገበው ሮይተርስ የሚኒስትሩን መታሰር ማረጋገጥ እንደማይችል ገልጻል፡፡ባለፈው ሳምንት የአለም አቀፍ የመድሃኒት ድርጅት ወኪል የሆኑት ደሊሽ ንጉዋያ በተማሳሳይ ምክንያት መታሰራቸው ተዘግቧል፡፡
የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ኢመርሰን ምናንጋግዋ ግዥውን መሰረዛቸው ታውቋል፡፡
በዚምባብዌ እስካሁን 500 ሰዎቸ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 4 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ከኮሮና ቫይረስ በተጨማሪ ሀገሪቱ ከፍተኛ በሚባል የኢኮኖሚ መግባቷና በተደጋጋሚ የህዝብ ቁጣን ሲያስነሳ ቆይቷል፡፡