ጃኮብ ዙማ የክስ ሂደታውን ከእስር ቤት ውጪ ሆነው እንዲከታተሉ ሊደረግ ነው
ጃብ ዙማ ጠበቆች ደንበኛቸው እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው “ኢ-ህገመንግስታዊ እና ህገ-ወጥ ድረጊት ነው” ብለዋል
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ዙማ እስር ቤት ከገቡ ሳምንታት ተቆጥረዋል
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ የክስ ሂደታቸውን ከእስር ወጥተው እንዲከታተሉ እንደተፈቀደላቸው ተሰምቷል።
ፕሬዚዳንቱ ከእስር ቤት እንዲወጡ የተፈቀደላቸው በመንግስት ቁጥጥር ስር ባለው የምርመራ ኮሚሽን ፊት በአካል እንዲቀርቡ በሚል እንደሆነም ነው የተገለጸው።
ዙማ የፊታችን ማክሰኞ እለት ፒተር ማርሚዚበርግ በሚገኝ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል።
ነሐሴ 4 ቀን በተሰጠ የፍርድ ቤት ትእዛዝ መሰረት የበፒተርማርሚዚበርግ ችሎት በክፍት የሚሆን ይሆናል፡፡
የዙማ ጠበቆች ድንበኛቸው እስካሁን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መቆየታቸው የመብት ጥሰት እንደሆነ በመግለጽ፤ ዙማ ፍድ ቤት እንዲቀርቡ አጥብቀው ሲታገሉ ቆይተዋል።
የዙማ ጠበቃ ለፍርድ ቤቱ ባስገቡት ባለ ሁለት ገጽ አቤቱታ “ድርጊቱ ኢ-ህገመንግስታዊ እና ህገ ወጥ ነው” ብለውታል።
የጠበቃው አቤቱታ ተከትሎም ዳኛው ምንም ማስረጃ ስለማይቀርብ ምርመራው በበይነ መረብ ሊከናወን ይችላል የሚለውን የቀድሞውን ውሳኔ እንደቀለበሱ ተገልጸዋል።
ዳኛው ሁሉም ሂደት የኮቪድ መመርያ በጠበቀና ባከበረ መልኩ እንዲከናወን ሲሉም አሳስቧል።
ዙማ እስር ቤት ከገቡ ሳምንታት ቢሆናቸውም መታሰራቸው ተከትሎ በክወዙሉ-ናታል እና ግዋተንግ ግዘቶች በተነሳው አመጽ የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈ ነው፡፡
በተፈጠረው አመጽ እስካሁን የ337 ህይወት ያለፈ ሲሆን፤ 213 ወንጀለኞች ወደ አድኖ ወደ ህግ የማቅረብ ሂደቱ በተጠናከረ ሁኔታ እየተሰራ መሆኑን የሀገሪቱ ባለስልጠናት በመግለጽ ላይ ናቸው።
አምነስቲ ኢንተርነሽናል በበኩሉ የተፈጸሙ ግድያዎችን በተመለከተ የተናጠል ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል።
የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛው ፍርድ ቤትም የ79 ዓመቱ ቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ፍርድ ቤት ለሚያደርገው የሙስና ወንጀል ምርመራ መረጃ ለመስጠት ሲጠየቁ በተደጋጋሚ ባለመተባበራቸው፣ ለፍርድ ቤቱ ንቀት አሳይተዋል በሚል የ15 ወራት የእስር ቅጣት እንዳሳለፈባቸው ይታወሳል።
ጃኮብ ዙማ ደቡብ አፍሪካን ከፈረንጆቹ 2009 እስከ 2017 ዓመት ድረስ በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ ቆይተው ከህዝብ በተነሳባቸው ተቃውሞ በአሁኑ የአገሪቱ ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሳ መተካታቸው ይታወሳል።