በጥቃቱ በትንሹ አምስት የግብፅ ጦር አባላት የሆኑ ወታደሮች ቆስለዋል
በግብፅ ስዊዝ ካናል ላይ በደረሰ የሽብር ጥቃት በትንሹ 11 ወታደሮች ተገደሉ።
በግብፅ ምስራቃዊ ስዊዝ ካናል ላይ ተፈጸመ በተባለ የሽብር ጥቃት በትንሺ 11 ወታደሮች መገደላቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።
በዚህ አደጋ ላይ በትንሹ አምስት የግብፅ ጦር አባላት የሆኑ ወታደሮችም ቆስለዋል ተብሏል።
ባሳለፍነው ሳምንት አንድ ተጠርጣሪ የሽብር ቡድን አባል ነው የተባለ ወጣት በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ያለ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ያጋየ ሲሆን የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር ተችሎ እንደነበር ዘገባው አክሏል።
የግብፅ መከላከያ ጦር ስለ አደጋው ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ከመስጠት የተቆጠበ ሲሆን ለዚህ አደጋ እስካሁን ሀላፊነት የወሰደ አካል እንደሌለ ተገልጿል።
የግብፅ ጦር አሁን ላይ አካባቢውን ተቆጣጥሮ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሆነም ተጠቅሷል።
ግብፅ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአሸባሪነት ከተፈረጀው እና በሲናይ በረሃ እንደመሸገ በሚገለጸው እሰላሚክ ስቴት ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጥቃቶችን በማስተናገድ ላይ ትገኛለች።
የእስላሚስት ስቴት የሽብር ቡድን ከፈረንጆቹ 2013 ዓመት ጀምሮ ከግብፅ መከላከያ ጦር ጋር በመዋጋት ላይ ሲሆን 2018 ላይ ባደረሰው የሽብር ጥቃት በርካቶች መሞታቸው ይታወሳል።