በአፍሪካ ዝቅተኛ ወንጀል የሚፈጸምባቸው 10 ከተሞች
ኑምቢዮ በተሰኘው የአለም አቀፍ ተቋም ጥናት የ17 የአፍሪካ ከተሞች የወንጀል ተጋላጭነት ደረጃ ይፋ ሆኗል
የኢትዮጵያ መዲናዋ አዲስ አበባ ዝቅተኛ ወንጀል ከሚፈጸምባቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት 4ኛ ደረጃን ይዛለች
የሀገራት ወይንም የከተሞች የወንጀል ተጋላጭነት ደረጃ ከህዝብ መጠናቸው አንጻር የተፈጸሙ ወንጀሎችን በማጥናት ይወጣል።
በ100 ሺህ ሰዎች መኖሪያ አካባቢ በተወሰነ የጊዜ ልዩነት የደረሱ የወንጀል ድርጊቶችን በመቁጠርም ደረጃው ይፋ ይደረጋል።
ሰዎች ጥቅጥቅ ብለው የሚኖሩባቸው አካባቢዎች ወንጀል ሲበራከትባቸው፥ የገጠር አካባቢዎች እና ሰዎች ተራርቀው የሚኖሩባቸው ከተሞች ደግሞ አነስተኛ የወንጀል ድርጊት ይፈጸምባቸዋል።
ኑምቢዮ የተሰኘው አለም አቀፍ ተቋም በየአመቱ የከተሞችን የወንጀል ተጋላጭነት ደረጃ ሲያወጣም ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ስሌትን ይጠቀማል።
የኑምቢዮ ድረገጽ ጎብኝዎች ለከተሞቹ የወንጀል ተጋላጭነት ከ2 እስከ ነጌቲቭ 2 ውጤት እንዲሰጡ ይደረጋል።
በዚህም አጠቃላይ ውጤቱ ከ20 እስከ 40 ከሆነ በጣም ዝቅተኛ፣ ከ40 እስከ 60 ከሆነ ዝቅተኛ፣ ከ60 እስከ 80 ከፍተኛ፣ ከ80 በላይ ከሆነ ደግሞ በጣም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣሉ።
ተቋሙ የ2022 የከተሞች የወንጀል ተጋላጭነት ደረጃ ሲያወጣ ታዲያ 17 የአፍሪካ ከተሞች በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል።
አስሩ ከተሞችም ዝቅተኛ ወንጀል የሚፈጸምባቸው ከተሞች ሆነው ተገኝተዋል ብሏል አፍሪካ ቢዝነስ ኢንሳይደር በዘገባው።
በአፍሪካ ዝቅተኛ ወንጀል የሚፈጸምባቸው 10 ከተሞች (የተሰጣቸው ነጥብ ጋር)
1. ሞሮኮ - ራባት - 36.1
2. ግብጽ - አሌክሳንድሪያ - 44.2
3. ቱኒዚያ - ቱኒስ - 47.4
4. ኢትዮጵያ - አዲስ አበባ - 49.2
5. ግብጽ - ካይሮ - 50
6. አልጀሪያ - አልጀርስ - 52.2
7. ሞሮኮ - ካዛብላንካ -54.8
8. ኬንያ - ናይሮቢ - 59
9. ዚምባቡዌ - ሃራሬ - 60.6
10. ሊቢያ - ትሪፖሊ - 62.1