የፎርብስ አስሩ የ2023 የአፍሪካ ቢሊየነሮች እነማን ናቸው?
የአፍሪካ 19 ቢሊየነሮች አጠቃላይ ሀብት 81 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር መድረሱን ፎርብስ ባወጣው መረጃ ጠቁሟል
የአህጉሪቷ ቢሊየነሮች ሀብት በ2022 የ3 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ቅናሽ ማሳየቱም ተገልጿል
ፎርብስ በቅርቡ የ2023 የአፍሪካ ባለጸጋዎችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
19 ቢሊየነሮችን ያካተተውን ዝርዝር ናይጀሪያዊው አሊኮ ዳንጎቴ በ13 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በቀዳሚነት ይመራሉ።
ላለፉት 12 አመታት የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሃብቱ ዳንጎቴ መሪነታቸውን ቢያስቀጥሉም ጠቅላላ ሃብታቸው ካለፈው አመት በ400 ሚሊየን ዶላር ቀንሷል ብሏል ፎርብስ።
የደቡብ አፍሪካው ጆናታን ሩፐርት ደግሞ በ10 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ዳንጎቴን ይከተላሉ።
ሌላኛው በከበሩ ማዕድናት ማውጣት ላይ የተሰማሩት ደቡብ አፍሪካዊ ኒኪ ኦፕንሄመር በ8 ነጥብ ቢሊየን ዶላር ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
የአፍሪካ 19 ቢሊየነሮች ድምር ሃብት 81 ነጥብ 8 ቢሊየን መሆኑንም ፎርብስን የጠቀሰው አፍሪካን ቢዝነስ ኢንሳይደርስ ዘግቧል።
ይህም በ2021 በ18 ቢሊየነሮች ከተመዘገበው የ84 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ሃብት የ3 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ቅናሽ ያሳየ ነው።
ለቅናሹም የአክሲዮኖች ዋጋ መውረድ በምክንያትነት ተጠቅሷል።
የፎርብስ አስሩ የ2023 የአፍሪካ ቢሊየነሮች
1. አሊኮ ዳንጎቴ (ናይጀሪያ)- 13 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር
2. ጆናታን ሩፐትርት (ደቡብ አፍሪካ) – 10 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር
3. ኒኪ ኦፐንሂሄመር (ደቡብ አፍሪካ) – 8 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር
4. አብዱልሰመድ ራቢዩ (ናይጀሪያ) – 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር
5. ናሴፍ ሳዊሪስ (ግብጽ) – 7 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር
6. ማይክ አዴኑጋ (ናይጀሪያ) – 5 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር
7. ኢሳድ ሬብራብ (አልጀሪያ) – 4 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር
8. ናጉይብ ሳዊሪስ (ግብጽ) – 3 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር
9. ፓትሪስ ሞስቴፕ (ደቡብ አፍሪካ) – 3 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር
10. ሞሃመድ መንሱር (ግብጽ) – 2 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር