ሰሜን አፍሪካዊቷ አልጀሪያ አልጀሪያ ቀዳ ስትሆን፤ ኢትዮጵያም በዝርዝሩ ተካታለች
በዓለማችን ካሉ አህጉራት መካከል በቆዳ ስፋቷ ሁለተኛ የሆነችው አፍሪካ የዓለም ሀያላን ሀገራት አይናቸውን ከጣሉባት ቆይቷል።
የዓለምን ልዕለ ሀያልነት መቆጣጠር የሚፈልጉ ሀገራት ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አፍሪካን ለመያዝ ብዙ መንገዶችን በመጠቀም ላይ ናቸው።
ዓለማችን ካሏት ሀብቶች መካከል በአፍሪካ ብቻ የሚገኙ ወይም ከሌሎች አህጉራት ጋር ሲነጻጸሩ አንደኛ የሚባሉ ብዙ ሀብቶችን የታደለችው የጥቁሮች አህጉር የምትባለው አፍሪካ የተቀረው ዓለም የሚደመምባቸው ብዙ ሀብቶችም ያሏት ሲሆን ለዛሬው በቆዳ ስፋታቸው 10 ቀዳሚ ሀገራትን ዝርዝር አዘጋጅተንላችኋል።
በአፍሪካ በቆዳ ስፋቷ አንደኛ የሆነችው ሰሜን አፍሪካዊቷ አልጀሪያ ስትሆን 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ስኩዬር ኪሎ ሜትር ስፋት አላት።
ከአልጀሪያ በመቀጠልም በመካከለኛው አፍሪካ የምትገኘው እና የበርካታ አምቅ ማዕድናት ባለቤት የሆነችው ዲሞክራቲክ ኮንጎ በ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ስኩዬር ኪሎ ሜትር ስፋት ሁለተኛዋ ሀገር ተብላለች።
ጎረቤት ሀገር ሱዳን እና በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው ሊቢያ በስፋታቸው የአፍሪካ ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃን የያዙ ሀገራት ናቸው።
ምዕራብ አፍሪካዎቹ ቻድ እና ኒጀር እያንዳንዳቸው በ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ስኪየር ኪሎ ሜትር ስፋት አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃን ሲይዙ አንጎላ እና ማሊም ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።
ደቡብ አፍሪካ በ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ስኩየር ኪሎ ሜትር ስፋት ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ የእኛዋ ኢትዮጵያም በ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ስኩየር ኪሎ ሜትር የቆዳ ስፋት በመያዝ 10ኛዋ የአፍሪካ ሀገር ነች።
ባላቸው የቆዳ ስፋት ከዓለም ቀዳሚ የሆነችው ሀገር ሩሲያ ስትሆን ካናዳ፣ አሜሪካ፣ ቻይና እና ብራዚል በቅደም ተከተላቸው ከ1ኛ እስከ 5ኛ ደረጃን የያዙ ሀገራት መሆናቸው ይታወቃል።