በአፍሪካ አማካኝ የእድሜ ጣራ በፈረንጆቹ 2000 እስከ 2019 ባለው ጊዜ ከ46 ወደ 56 ከፍ ብሏል
የዓለም ባንክ በአፍሪካ ያለው የሰዎች አማካኝ የእድሜ ጣሪያ ለተከታታይ 10ኛ ዓመት እድገት ማሳየቱን በያዝነው ወር ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል።
ለአብነትም በፈረንጆቹ ከ2000 እስከ 2019 ባለው ጊዜ በአፍሪካ የነበረው አማካኝ የእድሜ ጣራ ከ46 ወደ 56 ከፍ ማለቱን ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ ይዞት በወጣው ሪፖርት አመላክቷል።
በአፍሪካ ያለው የእድሜ ጣራ ከስፍራ ስፍራ ከፍተኛ የሆነ ልዩነት ያለው ሲሆን፤ ለልዩነቱ ዋነኛ ምክንያቶችም የጤና አገልግሎት ተደራሽነት፣ የኢኮኖሎ እድገት እና የበሽታ መስፋፋት ተጠቃሽ ናቸው።
እንደ ዓለም ባንክ ሪፖርት ከሆነ በአፍሪካ ከከፍተኛው እስቀ ዝቅተኛው የእድሜ ጣሪያ ያለ ሲሆን፤ ቀጥሎ የተዘረዘሩ 10 ሀገራት እንደ ቅደም ተከተላቸው ከፍተኛው የእድሜ ጣሪያ የተመዘገበባቸው ሀገራት ናቸው።
1. አልጄሪያ የእድሜ ጣራ 76.4 ዓመት
2. ሞሮኮ የእድሜ ጣራ 74 ዓመት
3. ቱኒዚያ የእድሜ ጣራ 73.8 ዓመት
4. ሞሪሽስ የእድሜ ጣራ 73.7 ዓመት
5. ሲሸልስ የእድሜ ጣራ 73.4 ዓመት
6. ሊቢያ የእድሜ ጣራ 71.9 ዓመት
7. ኬፕ ቨርዴ የእድሜ ጣራ 71.1 ዓመት
8. ግብጽ የእድሜ ጣራ 60.2 ዓመት
9. ሴኔጋል የእድሜ ጣራ 67.1 ዓመት
10. ኤርትራ የእድሜ ጣራ 66.5 ዓመት