በአፍሪካ አማካኝ የእድሜ ጣራ በፈረንጆቹ 2000 እስከ 2019 ባለው ጊዜ ከ46 ወደ 56 ከፍ ብሏል
የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ ያለው የሰዎች አማካኝ የእድሜ ጣሪያ ለተከታታይ 10ኛ ዓመት እድገት ማሳየቱን በያዝነው ወር ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል።
ለአብነትም በፈረንጆቹ ከ2000 እስከ 2019 ባለው ጊዜ በአፍሪካ የነበረው አማካኝ የእድሜ ጣራ ከ46 ወደ 56 ከፍ ማለቱን ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ ይዞት በወጣው ሪፖርት አመላክቷል።
በአሁጉሪቱ የሰዎች አማካኝ የእድሜ ጣሪያ መሻሻሎችን ማሳየት የቻለው የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት በመጨመሩ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፤ በፈረንጆቹ በ2000፤ 24 በመቶ የነበረው የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ተደራሽነት በ2019 ላይ ወደ 46 በመቶ ከፍ ማለቱም ተነግሯል።
እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ከሆነ በአፍሪካ ከከፍተኛው እስቀ ዝቅተኛው የእድሜ ጣሪያ ያለ ሲሆን፤ ቀጥሎ የተዘረዘሩ 15 ሀገራት እንደ ቅደም ተከተላቸው ከፍተኛው የእድሜ ጣሪያ የተመዘገበባቸው ሀገራት ናቸው።
1. አልጄሪያ የእድሜ ጣራ 77 ዓመት
2. ሞሮኮ የእድሜ ጣራ 74 ዓመት
3. ኬፕ ቬርዴ የእድሜ ጣራ 74 ዓመት
4. ቱኒዚያ የእድሜ ጣራ 74 ዓመት
5. ሞሪሽስ የእድሜ ጣራ 73 ዓመት
6. ሊቢያ 7የእድሜ ጣራ 72 ዓመት
7. ሲሸልስ የእድሜ ጣራ 71 ዓመት
8. ግብጽ የእድሜ ጣራ 70 ዓመት
9. ሳኦቶሜ ፕሪንሲፔ የእድሜ ጣራ 68 ዓመት
10. ሴኔጋል የእድሜ ጣራ 67 ዓመት
11. ሩዋንዳ የእድሜ ጣራ 67 ዓመት
12. ታንዛኒያ የእድሜ ጣራ 66 ዓመት
13. ኤርትራ የእድሜ ጣራ 66 ዓመት
14. ቦትስዋን የእድሜ ጣራ 65 ዓመት
15. ጋቦን የእድሜ ጣራ 65 ዓመት