አየርመንገዶች ተፎካካሪ ለመሆን ቢሊየን ዶላሮችን በማውጣት አዳዲስ አውሮፕላኖችን በመግዛት ላይ ይገኛሉ
ቱሪዝም እና ንግድ እየተስፋፋባት በምትገኘው አፍሪካ የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ከፍተኛ ድርሻ እየተወጣ ነው።
የቦይንግ ትንበያ እንደሚያሳየው በአህጉሪቱ ውስጥ ለመንቀሳቀስ የአየር ትራንስፖርትን ምርጫቸው የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር በሁለት አስርት አመታት ውስጥ በአራት እጥፍ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህም የአፍሪካ የአቪየሽን ኢንዱስትሪ በአለማቀፍ ደረጃ ፈጣን እድገት ከሚያሳዩት ተረርታ ያሰልፈዋል።
የአፍሪካ አየር መንገዶች ማህበር (አፍራ) መረጃ እንደሚያሳየው የአህጉሪቱ አየርመንገዶች በ2024 98 ሚሊየን መንገደኞችን ያጓጉዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በአፍሪካ 357 አየርመንገዶች ቢኖሩም ከጠቅላላው መንገደኛ 60 በመቶውን የሚያጓጉዙት ምርጥ 10 አየር መንገዶች ናቸው።
ይህም አብዛኞቹ የአህጉሪቱ አየርመንገዶች ጥቂት አውሮፕላን እና በቂ መሰረተ ልማት ያላሟሉ መሆናቸውን ያሳያል ብሏል አፍራ።
አቅማቸው ዝቅ ያለውም ሆነ ምርጥ 10ሩ አየርመንገዶች አዳዲስ አውሮፕላኖችን በመግዛት ተፎካካሪ ለመሆን ጥረት እያደረጉ ነው።
በ2023 ከ6 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ያገኘው የአፍሪካ ቀዳሚው አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየርመንገድ በዚህ አመት ከቦይንግ እና ኤርባስ ጋር የተፈራረማቸው የአውሮፕላን ግዥ ስምምነቶችም ለዚህ ማሳያ ናቸው።
በፕሌን ስፖተርስ ድረገጽ መረጃ መሰረት በርካታ አውሮፕላኖች ያሏቸውን ሀገራት ዝርዝር ይመልከቱ፦