ከፍተኛ የኮሌራ ወረርሽኝ ስርጭት እና ሞት ያለባቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት
በአፍሪካ 18 ሀገራት የኮሌራ ወረርሽኝ በርትቶባቸዋል
ከ16ሺህ በላይ ተጠቂዎች የሚገኙባት ኢትዮጵያ በአራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች
አፍሪካን ጨምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ስርጭቱ እያደገ የሚገኝው ኮሌራ የበርካታ ሰዎችን ህይወት እየነጠቀ ነው፡፡
ከንጽህና ጉድለት እና ከንጹህ መጠጥ ውሀ እጥረት እንደሚከሰት የሚነገረው ኮሌራ በተለይ ግጭት እና መፈናቀል ባለባቸው ሀገራት ስርጭቱ በርትቷል፡፡
በ2024 አመት 23.6 ሚሊየን ዜጎች የተፈናቀሉበት የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና በበሽታው ክፉኛ ከተመቱ የአለም ክፍሎች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ እስከ 4 ሚሊየን የሚደርሱ ሰዎች በበሽታው ሲጠቁ ከ21ሺህ እሰከ143 ሺህ ሰዎች በአመት በበሽታው ህይወታቸውን ያጣሉ
የአለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመላክተው በአፍሪካ በ18 ሀገራት ኮሌራ የተስፋፋ ሲሆን ከፈረንጆቹ ጥር 1 - ግንቦት 26 ድረስ በተሰበሰቡ መረጃዎች በአህጉሪቷ 92 ሺህ 789 የኮሌራ ታማሚዎች ተመዝግበዋል፡፡
በተመሳሳይ ጊዜ በ12 ሀገራት 1658 ሞት በ12 ሀገራት መከሰቱን የገለጸው የአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት በስርጭት ደረጃ 20ሺህ 113 ታማሚዎች የተገኙባት ዛምቢያ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ስትሆን ዚምቧቡዌ ፣ዲአር ኮንጎ እና ኢትዮጵያ በደረጃ ይከተላሉ፡፡