ዲ አር ኮንጎ 2 ሚልዮን ለሚሆኑ ዜጎቿ የኮሌራ ክትባት ዘመቻ ጀመረች
ለስድስት ቀናት በሚደረገው ክትባት የመስጠት ዘመቻ 3 ሺህ 600 የጤና ባለሙያዎች መሰማራታቸውን ተገልጿል
በኮንጎ 8 ሺህ 279 የኮሌራ ተጠርጣሪዎች እንዳሉ የዓለም ጤና ድርጅት የተገኘ መረጃ ያመለከታል
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሀገሪቱ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሺኝ ለመግታት በሶስት ግዛቶች ለሚገኙ 2 ሚሊዮን ዜጎች ላይ የኮሌራ የክትባት ዘመቻ ጀመረች።
ዘመቻው በወረርሽኙ በጣም የተጎዱትን በሃው-ሎማሚ፣ ደቡብ ኪቩ እና ታንጋኒካ ግዛቶች የሚገኙ 13 ዞኖች እንደሚሸፍንም ነው የሲጂቲኤን ዘገባ የሚያመለክተው፡፡
ለስደስት ቀናት በሚደረገው ክትባት የመስጠት ዘመቻ የማህበረሰብ ንቅናቄ የሚፈጥሩን ጨምሮ 3 ሺህ 600 የጤና ባለሙያዎች መሰማራታቸውንም ነው የተገለጸው፡፡
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ በጠቅላላው 8 ሺህ 279 የኮሌራ ተጠርጣሪዎች እንዳሏትና እና በ153 የሀገሪቱ 26 ግዛቶች ውስጥ 153 ሰዎች እንደሞቱባት የዓለም ጤና ድርጅት የተገኘ መረጃ ያሳያል።
በኮነጎ አለም ጤና ድርጅት ሀላፊ ዶ/ር አሜዲ ፕሮስፐር ጂጊምዴ “ኮሌራ ካልታከመ በሰአታት ውስጥ የሚገድል አደገኛ ኢንፌክሽን ነው፣ነገር ግን አስቀድሞ ሊተነበይ የሚችል እና መከላከል የሚቻል ነው፤ በሽታውን ለመከላከል ከሚረዱት ክትባቶች በተጨማሪ ንፁህ ውሃ በማቅረብ እና የንፅህና አጠባበቅን በማጠናከር ወረርሽኙን የበለጠ ለመከላከል እየሰራን ነው” ብሏል፡፡
ኮነጎ ይህንን የኮሌራ ክትባት ዘመቻ ስታደርግ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፤ 1.4 ሚለዮን ሰዎቸ ያዳረሰው የመጀመሪያው ዙር ክትባት ባለፉት መጋቢት እና ሃምሌ ማካሄዷ የሚታወስ ነው፡፡
ኮሌራ በተበከለ ውሃ ወይም ምግብ የሚተላለፍ በጣም ተላላፊ በሽታ መሆኑ ይተወቃል፡፡