አብዛኞቹ የባትሪ እድሜን የሚያሳጥሩ መተግበሪያዎች የማህበራዊ ሚዲያዎች እንደመሆናቸውም መፍትሄዎች ተጠቁመዋል
በየእለቱ የምንጠቀምባቸው የማህበራዊ ትስስር ገጽ መተግበሪያዎች የስማርት ስልኮቻችን ባትሪ በመጨረስ ቀዳሚ ሆነው ቀጥለዋል።
አይፒክላውድ የተሰኘ ተቋም ያደረገው ጥናትም የስማርት ስልኮችን ባትሪ እድሜ ከሚያሳጥሩ 20 መተግበሪያዎች ስድስቱ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መሆናቸውን ያሳያል።
የምንገኝበትን አቅጣጫ የሚጠይቁ፣ ዋይፋይ፣ ካሜራ፣ ማይክራፎንና ሌሎች ነገሮችን ለመጠቀም ፍቃድ የሚጠይቁ መተግበሪያዎች የስልክን ባትሪ በመጨረስ ቀዳሚዎቹ ሆነዋል።
አይፒክላውድ ይፋ ያደረጋቸው የስማርት ስልኮችን ባትሪ ይጨርሳሉ የተባሉ መተግበሪያዎች የሚከተሉት ናቸው፦
1. Fitbit
2. Uber
3. Skype
4. Facebook
5. Airbnb
6. Instagram
7. Tinder
8. Bumble
9. Snapchat
10. WhatsApp
ከተጠቀሱት መተግበሪያዎች ውስጥ አብዛኞቹን በየእለቱ የምንጠቀማቸው እንደመሆናቸው ልናጠፋቸው አንችልም የሚለው አይፒክላውድ፥ የማንጠቀምባቸው ከሆነ ማጥፋት ካልሆነ ግን አጠቃቀማችን ማስተካከል እንደሚገባ ያሳስባል።
“ፊትቢት” የተሰኘው መተግበሪያ ከሚሰጣቸው 16 አገልግሎቶች 14ቱ አጥፍተናቸውም ስራቸውን የሚቀጥሉ መሆኑ የስልክ ባትሪን በመጨረስ ቀዳሚው መተግበሪያ አድርጎታል።
ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ስናፕቻት፣ ዩትዩብ፣ ዋትስአፕ እና ሊንክድንም በተመሳሳይ የስማርስ ስልክ ባትሪ ቀበኛ ናቸው ይላል የአይፒክላውድ ጥናት።
የኦንላይን የፍቅር አጋር መፈለጊያዎች እና የጉዞ መተግበሪያዎችም እንዲሁ የስልካችን ባትሪ ክፉኛ ከሚበሉት መካከል ተጠቅሰዋል።
እናም አስፈላጊ ያልሆኑና ደጋግመን የማንጠቀምባቸውን መተግበሪያዎችን ከማጥፋት ባሻገር የሚከተለውን መንገድ በመጠቀም መተግበሪያዎቹ በውስጥ ስራቸውን እንዳይቀጥሉ በማድረግ የስልካችን ባትሪ እድሜ ማስረዘም ይቻላል።
“Apps” – “ባትሪ ይበላብናል ብለን የምናስበው መተግበሪያ ላይ መጨን “– “Battery” – “Allow background activity” የሚለውን አማራጭ ኦፍ ማድረግ
ሌላኛውን መንገድም ከታች በተቀመጠው ምስል ይመልከቱ፦