ስማርት ስልኮችን ተፈላጊ እያደረጉ ከመጡ ነጥቦች ውስጥ ፍጥነት፣ የካሜራ ጥራትና የመረጃ ማከማቻ ተጠቃሽ ናቸው
በ2022 ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን በላይ ስማርት ስልኮች የተሽጡ ሲሆን፥ አጠቃላይ የስማርት ስልኮች ተጠቃሚዎች ቁጥርም ከ6 ቢሊየን በላይ መድረሱን መረጃዎች ያሳያሉ።
በኢትዮጵያም የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎ ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ የመጣ ሲሆን፤ ስማርት ስልክ ለመግዛት ከመወሰናችን በፊት እነዚህን ነጥቦች ልብ ማለት ያስፈልጋል።
ስክሪን
ስክሪን ስማርት ስልኮችን በምንጠቀምበት ጊዜ ወሳኙ ክፍል ሲሆን፤ የስክሪኑ የጥራት መጠን እና ስፋት ደግሞ እንደአጠቃቀማችን ለሊለይ ይችላል።
በተለይም በስማርት ስልካችን ፎቶግራፍ እና ቪዲዮ ለማንሳት፣ ኤዲት ለማድረግ እና ለማስተላፍ እንዲሁም ለመመልከት በብዛት የምንጠቀም ከሆነ የስማርት ስልኩ ስክሪን “Full HD” አሊያም “QHD” ጥራት ያለከው እንዲሁም የስክሪኑ ስፋት ደገሞ እስከ 6 ኢንች ስፋት ያለው ቢሆን ይመከራል።
ባትሪ
የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች አብዝተው የሚያማርሩት ጉዳይ የባትሪው ወይም ቻርጅ የቆይታ አቅም ሲሆን፤ የስማርት ስልክ አምራቾችም ይህንን ለማስተካከል በየጊዜው አዳዲስ የባትሪ አቅም ይፋ እያደረጉ ነው።
የስማርት ስልካችን የባትሪ ቆይታ እንደ አጠቃቀማችን የሚወሰን ቢሆንም፤ ስማርት ስልክ አብተን የምንጠቀም ከሆነ ስማርት ስልኩን ስንገዛ የባትሪው አ3500Ah መሆኑን ብናረጋግጥ ይመከራል።
ኦፕሬቲንግ ሲስተም
ነስማርት ስልኮች ላይ የጎግል አንድሮይድ ኦትሬቲንግ ሲስተም እና የአፕል ኩባንያ አይፎን ኦፕሪቲንግ ሲስተም (አይ.ኦ.ኤስ) በስፋት የሚታወቁ ሲሆን፤ ሁዋዌይ በቅርቡ ሀርሞኒ የተባለ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም።
ኦፕሬቲንግ ሲስተም ስማርት ስልክ በምንገዛበት ወቅት ልብ ልንላቸው ከሚገቡ ነጥቦች ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ለአጠቃቀም ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ መልካም ነው።
ካሜራ
ስማርት ስልክ ግዢ ላይ የማሻሻጫ ነጥብ እየሆነ ከመጣው ውስጥ የካሜራ ጥራት ደረጃ አንዱ እየሆነ ይገኛል።
ከዋነኞች የስማርት ስልክ አምራቾች አፕል እና ሳምሰንግ ጀምሮ እስክ ጎግል እንዲሁም ሌሎችም የስማርት ስልኮች አሁን አሁን ካሜራዎቻው በሚያነሷቸው ከፍተኛ ጥራት ያለው ምስል ተመራጭ እየሆኑ መጥተዋል። ስለዚህ ስማረት ስልክ ስንገዛ የካሜራውን ጥራት ከግምት ማስገባት ይመከራል።
ስቶሬጅ (የመረጃ ማከማቻ)
የስማርተ ስልኮች የመረጃ ማከማቻ በጊጋ ባይት የተለያዩ መጠን ያላቸው ሲሆን፤ ስማርት ስልክ መንገዛበት ወቅት ስማርት ስልኩ በኦፕሬቲንግ ሲስተም ቀደም ብለው የተጫኑ መተግበሪያዎችን እንዲሁም አዳዲስ መተግበሪያዎችን በመንግጭመን ጊዜ ለመጠቀም የሚያስችል መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል
በተጨማሪም የድምጽ ማናገሪያ እና ስፒከር ጥራት እንዲሁም እንደ አሻራ፣ የይለፍ ቃል እና ሌሎችም የደህንነት ማራጭ ያለው መሆኑን ማረጋገጥም አስፈላጊ እንደሆነ ይነገራል።