በየሁለቱ ኩባንያዎች 10 ስማርት ስልክ ሞዴሎች ያስመዘገቡት ሽያጭ የ20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል
የአፕል ምርት የሆኑ አይፎን ስማርት ስልኮች በአለማቀፍ ደረጃ ሽያጫቸው ጨምሯል።
ባለፈው አመት ለገበያ ከቀረቡ ስማርት ስልኮች ከፍተኛውን ሽያጭ በማስመዝገብም ቀዳሚ ሆኗል ብሏል ካውንተርፖይንት የተባለ የጥናት ተቋም በድረገጹ ባሰፈረው መረጃ።
በየወሩ ለሽያጭ የቀረቡ ስማርት ስልኮችን መረጃ የሚከታተለው ካውንተርፖይንት እንዳስታወቀው በ2023 ከፍተኛ ሽያጭ ካስመዘገቡት 10 የስማርት ስልክ አምራቾች ውስጥ ሰባቱ የአፕል ምርቶች ናቸው።
አፕል ሰባት የስማርት ስልክ ሞዴሎች በርካታ ሽያጭ አስመዝግበው በምርጥ 10 ውስጥ ሲገቡ ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።
ቀሪ ሶስቱ በብዛት የተሸጡ ስማርት ስልኮች የደቡብ ኮሪያው ሳምሰንግ ኩባንያ ምርት መሆናቸው ተጠቅሷል።
በ2023 ከፍተኛ ሽያጭ በማስመዝገብ ቀዳሚውን ደረጃ የያዘው አይፎን 14 ስማርት ስልክ ነው።
አይፎን 14 ከአፕል ስልኮች ሽያጭ 19 በመቶ፤ ከጠቅላላው አለማቀፍ የስማርት ስልኮች ሽያጭ ደግሞ 3 የ3 ነጥብ 9 በመቶ ድርሻ አለው ብሏል ካውንተርፖይንት በድረገጹ።
ባለፈው አመት ከፍተኛ ተቀባይነትና ሽያጭ የነበራቸውን ስማርት ስልኮች ይመልከቱ፦