ቻይና፣ ሳኡዲ አረቢያ እና ማሌዥያ ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል
የካናዳው ማክጊል ዩኒቨርሲቲ ዜጎቻቸው በስማርት ስልክ ሱስ የተጠመዱ ሀገራትን ይፋ አድርጓል።
የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች ከ2014 እስከ 2020 የሀገራት የስማርት ስልክ አጠቃቀም መረጃን መሰረት ያደረገ ጥናት አድርገዋል።
በ24 ሀገራት የሚገኙ 34 ሺህ ሰዎች በተሳተፉበት ጥናት ቻይና የአለማችን የስማርት ስልክ ሱሰኞች በብዛት የሚገኙባት ሀገር ተገኝታለች።
ሳኡዲ አረቢያ እና ማሌዥያ ቤጂንግን በመከተል ዜጎቻቸው ከስልካቸው ለመነጠል የሚከብዳቸው ሀገራት ሆነዋል ይላል ጥናቱ።
የስማርት ስልኮችን ለምን ያህል ስአት ይጠቀማሉ የሚለውን ከ60 ነጥብ በመስጠት ይፋ የተደረገውን ደረጃ ይመልከቱ፦