በዝቅተኛ ወጪ ልንሄድና ልንዝናና የምንችልባቸው 10 የዓለም ሀገሮች በ2022
በርካታ ጊዜ ሰለ ጉዞ ስናስብ የወጪ ጉዳይ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል
ቱርኪዬ፣ ታይላንድና ሮማኒያ በዝቅተኛ ወጪ ልንዝናናባቸው ከምንችልባቸው ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው
በርካታ ጊዜ ሰለ ጉዞ ስናስብ አእምሯችን ላይ ቀድሞ ከሚመጡት ውስጥ የወጪ ጉዳይ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።
ማንኛውም ሰው ቢሆን በአነስተኛ ወጪ ቢዝናና የሚጠላ የለም እኛም `ፐረሮጀክት ኢንስፖ` የተባለ ድረ ገጽ በዝቅተኛ ወጪ ልንሄድና ልንዝናና የምንችልባቸው በሚል የዘረዘራቸውን 10 ሀገራት እንዲህ አቅርበናል።
1. ኒካሯጓ
ኒካሯጓ በመካከለኛ አሜሪካ የምትገኝ ሀገር ሲሆን ባለቀለም ከተሞቿ፤ የውኃ ላይ መዝኛዎቿ እና ባህላዊ አኗኗራ በጎብኚዎች እንደትመረጥ እንዳደረጋት ይነገራል።
ከሁሉም በላይ ግን በሀገሪቱ ኑሮ ለጎብኚዎች ርከሻ መሆኑ እና በሀገሪቱ ለማሳለፍ የሚጠይቀው ወጪ ዝቅተኛ በመሆኑ ተመራጭ እንዳደረጋት ይነገራል።
በሀገሪቱ ሁለት ክፍል ያለው እና የራሱ መታጠቢያ ያለው ውድ ሆቴል ለመያዝ 25 የአሜሪካ ዶላር ብቻ የሚያስፈልግ ሲሆን፤ በመደበኛ የሆቴል ክፍሎችን ከ5 እስከ 12 ዶለር ብቻ በቂ ነው።
ከመንገድ ዳር ምግብ እስከ 2 ዶላር ይገኛል የተባለ ሲሆን በሬስቶራንቶች ውስጥ ገብቶ መገልገል ለሚፈልግ ሰው ደግሞ የአንድ ምግበ ዋጋ ከ3 እስከ 5 ዶላር ብቻ ነው ተብሏል።
2.ቱርክ (ቱርኪዬ)
ቱርክ ባላት የምእራቡ እና የመስራቁ ዓለም የተቀላቀለ የኑሮ ዘይቤ እንዲሁም ባላት የመሬት እንዲሁም በምግቦቿ እና በባህር ዳርቻዎቿ በቱሪስት ተመራጭ ያደርጋተል።
በሀገሪቱ የሚገኙ አባዛኛዎቹ ሆቴሎች በቀን ቆይታ ከ20 እስከ 30 ዶላር ብቻ የሚያስከፍል ሲሆን፤ በሀገሪቱ ምግብ እና ትራነስፖርትን በዝቅተኛ ዋጋ ማግኘት መቻሉም በዝቅተኛ ዋጋ ለንዝናናባቸው ከምችለው ሀገራት መካከል እንድትሆን ድርጓታል።
3. ስሪላንካ
ስሪላንካም በዝቅተኛ ወጪ ለመዘውናናት ከሚመረጡ ሀገራት መካከል የምትገኝ ሲሆን፤ በከተማዋ ውስጥ ባሉ የባህር ዳርቻ ሬስቶራንቶች እና ካፌዎች ለመግለግለ በቀን 20 ዶላር ብቻ በቂ ነው።
ምግብ በካፌዎች ውስጥ ከ2 እስከ 3 ዶላር ማገኘት የሚቻል ሲሆን፤ ቆንጆ ምልከታ ያለውን የሆቴል ክፍል በቀን በ20 ዶላር ማግኘት ይቻላል።
4. ካምቦዲያ
ካምቦዲያ በታሪክ ሀብታም የሆነች፤ በጣም ጣፋጭ ምግብ እና አዝናኝ የምሽት ጊዜ ማግኘት የሚቻልባት እንደሆነ ይገርላታል።
በሀገሪቱ በሚገኙ መደበኛ ሬስቶራንቶች ከ1 እስከ 3 ዶላር መካከል ምግብ ማግኘት ይቸላል የተባለ ሲሆን፤ የመኝታ ክፍሎችን ከ6 እስከ 8 ዶላር እንዲሁም፤ አይ ደረጃ ያለው ሆቴል ነው የማርፈው ለሚል ሰው ደግሞ ከ15 እስከ 20 ዶላር ማግኘት ይቻላል።
5. ኔፓል
በካታማዱ ከተማ አካባቢ ለመቆየት የአፈለገ አንድ ሰዎ ሆቴል ከ5 ዶላር አንስቶ እስከ 25 ዶላር ማግኘት የሚቻል ሲሆን፤ በመደበኛ ሬስቶራንቶች ውስጥ ምግብ መመገብ የፈለገ ሰው አንድን ምግብ ከ2 እስከ 4 ዶላር ማግኘት ይቻላል።
6. ታይላንድ
ታይላንድ ርካሽ ናት…? በሎ ለሚጠይቅ ሰው በእርግጠኝነት አው ብሎ መናገር ይቻላል። የሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ግን በእርግጠኝነት ከባንኮክ እና ደሴቶች የበለጠ ርካሽ ነው።
በታይላንድ አልጋ ለመያዝ በከተማ ውስጥ በ7 ዶላር፤ በገጠር ውስጥ በ4 ዶላር ርካሽ ክፍል ማግኘት ይቻላል የተባለ ሲሆን፤ በደሴቶቹ ላይ ከሆኑ ወይም አየር ማቀዝቀዣ ክፍል ከፈለጉ በአዳር ቢያንስ 17 ዶላር ይከፍላሉ።
የረሃብ ስሜት ከተመዎትም፤ የጎዳና ላይ አንድ ምግብ እስከ 0.65 ዶላር፣ እና በአካባቢውበሚገኝ ሬስቶራንት ለመብላት ከወሰኑ ከ3-5 ዶላር አካባቢ ሊያስወጣዎት ይችላል።
7. ፔሩ
ፔሩ ከደቡብ አሜሪካ በጣም ተመራጭ ሀገራት አንዷ ስትሆን ርካሽ መጠለያ በብዛት የሚገኝባ ነች፣ በሆስቴል መኝታ በአዳር ከ8-15 የአሜሪካ ዶላር አካባቢ፣ የደረጃቸውን በጠበቁ ሆቴሎች በአዳር ከ30-50 የአሜሪካ ዶላር አካባቢ ይጀምራሉ።
በጣም ርካሹን ምግብ በመንገድ ዳር በሚገኙ ድንኳኖች እና በገበያዎች አካባቢ አንድ ምግብ ከ1-2 ዶላር ማግኘት የሚቻል ሲሆን፤ አይ ሬስቶራንት ነው የምጠቀመው ካልን ደግሞ ከ4-6 ዶላር አካባቢ ማግኘት ይቻላል።
8. ኢንዶኔዥያ
በስነሰለታማ ደሴቶች፣ በእሳተ ገሞራ የተፈጠሩ ተለያዩ የአለት ቅስጾች፣ ታሪካዎ ቦታዎቿ እንዲሁም በቀን እና በማታ ማራኪ እይታ ባላቸው የባህር ዳርቻዎቿ ትታወቃለች።
በኢንዶኔዥያ በሆስቴል ወይም በእንግዳ ማረፊያ ውስጥ ለሁለት ክፍል ከ2 እስከ 4 ዶላር የሚያስከፍል ሲሆን፤ በባሊ ወይም በታዋቂው የኢንዶኔዥያ የቱሪስት ደሴቶች ላይ የአየር ማቀዝቀዣ ያላቸው ክፍሎች ለሁለት ሰዎች በአዳር ከ11-17 ዶላር አካባቢ ያስከፍላሉ።
የጎዳና ላይ ምግብ ከ0.50-2 ዶላር ዋጋ ያለው ሲሆን፤ በአካባቢው በሚገኝ ሬስቶራንት ውስጥ ለመጠቀም ከፈለጉ፣ ለአንድ ምግብ ከ2-6 ዶላር አካባቢ ያስወጣል።
9. ሮማኒያ
በታሪክ፣ በሥነ ጥበባት እና በሥዕላዊ ውበት የበለፀገችው ሮማኒያ በእርግጠኝነት በዝቅተኛ ወጪ መዝናናት ለሚፈልጉ ጎብኚዎች ተመራጭ ስፍራ ነች።
በሆስቴል ውስጥ የመኝታ ክፍል አልጋ በአዳር ከ8 እስከ 12 ዶላር ማያዝ የሚቻል ሲሆን፤ ውድ የተባሉ ሆቴሎች ማረፍ ለሚፈልግ ሰው መነሻ ዋገው40 ዶላር አካባቢ ነው።
በሮማኒያ በአብዛኛው በአነስተኛ ዋጋ የሚገኝ ምግብ $5 ዶላር የሚሸጥ ሲሆን፣ እንደ ብራሶቭ ወይም ሲጊሶራ ባሉ ዋና ዋና የቱሪስት ከተሞች ያሉ ምግብ ቤቶች ትንሽ ውድ እና ከ15-25 የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ያስከፍላሉ።
10. ደቡብ አፍሪካ
የዱር አራዊት መመልከቻ፣ ምቹ የህዝብ እና የመጓጓዣ አማራጮችን ንዲሁም በነጻ የሚጎበኙት የሀገሪቱ ድንቅ ሙዚየሞች በደቡብ አፍሪካን ተመራጭ ካደረጉት ውስጥ ይገኛ።
ከወጪ አንጻርም በዝቅተኛ ዋጋ መዝናናት ከሚቻልባቸው ሀገራት ውስጥ የተካተተችው ደቡብ አፍሪካ በሆቴል ውስጥ አልጋ ከ10 ዶላር ጀምሮ ማግኘት ይቻላል ተብሏል።
በፈጣን ምግብ ወይም ተራ ምግብ ቤት ውስጥ ያለ ቀላል ምግብ ከ4-7 የአሜሪካ ዶላር ማግኘት የሚቻል ሲሆን በሬስቶራንት ውስጥ ቁጭ ብለው መመገብ ከፈለጉ ደግሞ ከ6-12 የአሜሪካ ዶላር ሊያወጣዎት ይችላል።