ታይዋን፣ 10 የቻይና አውሮፕላኖች የባህር አካሏን መካከለኛ መስመር አቋርጠዋል ስትል ከሰሰች
ቻይና በነሐሴ ወር ላይ የጦርነት ልምምዶችን በታይዋን ዙሪያ ማካሄድ የጀመረችው የአሜሪካ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታይፔን ከጎበኙ በኋላ ነበር
10 የቻይና አውሮፕላኖች የታይዋን ባህርን አማካኝ መስመር ማቋረጣቸውን የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል
የቻይና አውሮፕላኖች የታይዋን ባህርን አማካኝ መስመር ማቋረጣቸውን የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።
ሚኒስቴሩ ቻይና በተለምዶ በሁለቱ ወገኖች መካከል መደበኛ ያልሆነ ድንበር በመሆን እያገለገለ ያለውን በማለፍ ቤጂንግ በደሴቲቱ አቅራቢያ ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን እያካሄደች ነው ብሏል።
ዘጠኝ የቻይና ተዋጊ ጄቶች እና አንድ ወታደራዊ ሰው አልባ ድሮን ቅዳሜ እለት መስመሩን አቋርጠዋል ሲል ሚኒስቴሩ የቻይና ወታደራዊ እንቅስቃሴን በሚመለከት ዕለታዊ ዘገባው ላይ ገልጿል።
ታይዋን የቻይናን አውሮፕላኖች ለማስጠንቀቅ አውሮፕላኖችን የላከች ሲሆን ሚሳይል ሲስተሙም ይከታተሏቸዋል ሲል ሚኒስቴሩ ለምላሹ መደበኛ ቃላትን ተጠቅሟል።
ቻይና የራሴ ግዛት ነች የምትላት ታይዋን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በምትመራው ደሴት አቅራቢያ በሚገኘው የቻይና አየር ኃይል የዕለት ተዕለት ተልእኮዎች መካከል በአብዛኛው በደቡብ ምእራብ የአየር መከላከያ መለያ ቀጣና ላይ በምታደርገው እንቅስቃሴ ቅሬታዋን ስታሰማ ቆይታለች።
ቤጂንግ አሁን በአሜሪካ አህጉር የሚጓዙት የታይዋን ፕሬዚደንት ጻይ ኢንግ ዌን የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ኬቨን ማካርቲን ቢገናኙ ያልተገለጸ አፀፋዊ ምላሽ እንደሚሰጥ ዝታለች።
ቻይና በነሐሴ ወር ላይ የጦርነት ልምምዶችን በታይዋን ዙሪያ ማካሄድ የጀመረችው የአሜሪካ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታይፔን ከጎበኙ በኋላ ነበር።
በፔሎሲ ጉብኝት የተበሳጨችው ቻይና በታይዋን ዙሪያ ለቀናት የቆየ ወታደራዊ ልምምድ ማድረጓ ይታወሳል።
የደሴቲቱን የፀጥታ እቅድ የሚያውቅ አንድ የታይዋን ከፍተኛ ባለስልጣን በዚህ ሳምንት ለሮይተርስ እንደተናገሩት ቻይና እንደዚህ አይነት ትላልቅ ልምምዶችን ትደግማለች ተብሎ ባይጠበቅም ቻይና "ምክንያታዊ ያልሆነ" ምላሽ ከሰጠች ሁሉም ዝግጅቶች ተደርገዋል።