ቻይና ጉብኝቱ ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች
በታይዋን የባህር ወሽመጥ ውጥረት ለምን ነገሰ?
በታይዋን ባህር ሰርጥ ላይ አዲስ ውጥረት ነግሷል።
የታይዋን የመከላከያ ሚነሰስቴር ዘጠኝ የቻይና አውሮፕላኖች ወሰነሰ እንዳቋረጡ አሳውቋል።
ተንታኞች እርምጃው የታይዋን ፕሬዝዳንት በአሜሪካ ጉብኝታቸው ቻይናን የሚያስቆጣ አዲስ ቅስቀሳ እንዳያደርጉ "የማስጠንቀቂያ ደወል" ነው ብለዋል።
የታይዋን ፕሬዝዳንት ታይ ኢንግ ዌን የኒውዮርክ ጉብኝት ቤጂንግን አስቆጥቷል።
ቻይና ፕሬዝዳንቷ ከአሜሪካ ምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ኬቨን ማካርቲ ጋር ከተገናኙ አጻፋውን እንደምትመልስ ተናግራለች።
ዋሽንግተን ጉብኝቱ “መሸጋገሪያ ብቻ ነው” በማለት የቤጂንግን ቁጣ አጣጥላለች።
ቤጂንግ "ለመዋጋት እየተዘጋጀች" መሆኑን የታይዋን የመከላከያ ሚንስቴር አስታውቋል።
ለውጊያ ዝግጁ ናቸው የተባሉ ዘጠኝ የቻይና አውሮፕላኖች የታይዋን "ባህርን መስመር" አቋርጠው መግባታቸውን ታይፔ ገልጻለች።
"የቻይና ድርጊት ሆን ተብሎ በታይዋን ባህር ውስጥ ውጥረትን ይፈጥራል" ብላለች።
የቻይና ተዋጊ አውሮፕላኖች የታይዋንን የባህር ወሽመጥ ማዕከል ሲያቋርጡ ይህ የመጀመሪያ አይደለም ተብሏል።
የቀድሞ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በደሴቲቱን ከጎበኙ ጀምሮ አውሮፕላኖቹ ተስተውለዋል ነው የተባለው።
ተጥሷል የተባለው መስመር ታይዋን እና ቻይናን በሚለያየው የባህር ዳርቻ መሃል የሚገኝ ነው።
ደሴቱ መደበኛ ያልሆነ ድንበር እንደሆ ትቆጥራለች። ቤጂንግ ግን ይህን አትቀበለውም።
ቻይና ታይዋን የግዛቷ አካል አድርጋ ስለምትቆጥር የታይፔን ማንኛውንም ዓለም አቀፍ ግንኙነት አትቀበልም።