ትራምፕና እስራኤል የጋዛ ነዋሪዎችን ለማስፈር እቅድ የያዝባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
የጋዛ ነዋሪዎችን ለማስፈር ራስ ገዞቹ ሶማሊላንድና ፑንትላድን ጨምሮ 10 ሀገራት ይፋ ተደርገዋል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/07/252-125830-whatsapp-image-2025-02-06-at-12.01.14-pm_700x400.jpeg)
ሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና ለማግኘት የጋዛ ተፈናቃዮችን ልትቀበል ትችላለች ተብሏል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጋዛ ጉዳይ ያዙት አወዛጋቢ እቅድ ከፍተኛ ውግዘት ቢያስከትልባቸውም ጸንተውበታል።
ፍልስጤማውያንን ከጋዛ አስወጥቶ ጋዛን የመቆጣጠር ፍጎላጎት እንዳላቸው የገለጹት ትራምፕ፤ የጋዛ ተፋናቃዮችን ለማስፈር ያቀዱባቸው ሀገረሰትም ይፋ እየተደረጉ ነው።
ትራምፕ የጋዛ ተፋናቃዮችን ለማስፈር ከመረጧቸው ሀገራት መካከል ግብጽ እና ዮርዳስን በስም ቢጠቅሱም ሌሎቹን ግን ይፋ አላደረጉም ነበር ተብሏል።
ሆኖም ግን የእስራኤል ባለስልጣናት ከግብጽ እና ዮርዳስ በተጨማሪ የጋዛ ነዋሪዎች እንዲሰፍሩባቸው የታቀዱ 8 ሀገራት እና በሶማሊያ ውስጥ የሚገኙ ሁለት ራስ ገዝ ክልሎችን ይፋ አድርገዋል።
የጋዛ ነዋሪዎችን ለማስፈር የመረጡ ሀገራትም
ዮርዳስ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ነዋሪዎችን በማስፈር ዙሪያ የዮርዳኖስን ስም ደጋግመው የሚያነሱ ሲሆን፤ በሚቀጥለው ሳምንት ዋሽንግተንን ከሚጎበኙት ከዮርዳኖሱ ንጉስ አብዱላህ 2ኛ ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ እንደሚነጋገሩ አስታውቀዋል።
ዮርዳኖስ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ መፈናቀል እቅድ በፍጹም ተቀባይነት የለውም በማለት ተቃውማለች።
-ግብፅ
ፕሬዝዳት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ነዋሪዎች በቋሚነት አሊያም በጊዝያዊነት በግብጽ እንደሚሰፍሩ በተደጋጋሚ ያነሱ ሲሆን፤ ግብፅም ፍልስጤማውያንን ከጋዛ መፈናቀል እቅድን ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጋለች።
-አልባኒያ
የእስራኤሉ ቻናል 12 እንዳወጣው ዘገባ ከሆነ አልባያ የጋዛ ተፈናቃዮች ይሰፍሩበታል ተብለው ከተለዩ ሀገራት መካከል አንዷ ነች።
የአልባያው ሚኒስትር በኤክስ ገጻቸው ላይ እንደዚህ አይት የውሸት ዜና ሰሜቹ አላውቅም፤ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ከሰሞኑ ብዙ ነገሮች ሲባሉ ሰምቻለሁ፤ ይህ ግን ፍጹ ውሸት ነው ብለዋል።
-ኢንዶኔዥያ
ኢንዶኔዢያ የጋዛ ነዋሪዎችን ለማዘዋወር ከታቀደባቸው ሀገራት መካከል አንዷ እንደሆነች የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ሆኖም ግን የኢንዶኔዤያ የውጭ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ፤ በዚህ ዙሪያ ከየትኛውም አካል እስካን የቀረበልኝ ጥያቄ የለም ሲል መረጃውን ውድቅ አድርጓል።
- ሶማሊላንድ
ራስ ገዟ ሶማላንድ የጋዛ ነዋሪዎችን ለማስፈር እቅድ ከተያዘባው አካባቢዎች ውስጥ እንደምትገኝ የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን መረጃ ያመለክታል።
ዓለም አቀፍ የሀገርነት እውቅናን የምትፈልገው ሶማሊላንድ እውቅና የሚሰጣት ከሆነ የጋዛ ነዋሪዎችን ልትቀብል እንደምትችል ተገምቷል።
- ፑንትላድ
ከሶማሊያ ማእከላዊ ምንግስ ጋር ግንኙነት በማቋረጥ በከፊል ራስ ገዝነቷን ያወጀችው ፑንት ላንድም የጋዛ ነዋሪዎችን ለማስፈር እቅድ ከተያዘባው አካባቢዎች ውስጥ እንደምትገኝ ነው የተገለጸው።
- ሞሮኮ
የእስራኤሉ ቻናል 12 ሞሮኮ ፍሊስጤማውያን ሊሰፍሩባቸው ከሚች ሀገራ መካከል ነች በሊም፤ ሞሮኮ ግን ፍልስጤማውያንን ከጋዛ መፈናቀል እቅድን ውድቅ አድርጋለች
በተጨማሪም ስፔን፣ አየርላንድ፣ ኖርዌይ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያም የጋዛ ነዋሪ ፍሊስጤማውያን ሊሰፍሩባው ይችላ ተብለው ከተለዩ ሀገራት መካከል ናቸው ተብሏል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ወደ ዋይትሃውስ እንደገቡ የጋዛ ፍርስራሽ እስኪጸዳ ድረስ ፍልስጤማውያን እንደ ግብጽ እና ዮርዳኖስ ባሉ ሀገራት እንዲጠለሉ ሃሳብ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ዶናልድ ትራምፕ ጋዛን ለመቆጣጠር የያዙትን እቅድ በርካታ የዓለም ሀገራ በመቃወም ላይ ይገኛሉ።
በትራምፕ ውሳኔ የተገረሙ እና የተደናገጡ የጋዛ ነዋሪ ፍሊጤየማውያን “ጋዛን ለቀን አንወጣም” ሲሉ ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል።
“ነፍሳችንን ቢያስከፍለን እንኳን ጋዛን አንለቅም” ያሉት ነዋሪዎቹ፤ “የትራምፕን ውሳኔ እንቃወማለን፣ ጦርቱን አስቁሟል፤ ነገር ግን እኛን ማፈናቀል ህይወታችን እንዲያበቃለት ያደርጋል” ብለዋል።
በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምት መደረሱን ተከትሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍሊስጤማውያን ወደ ፈራረሰቸው መንደራው እየተመሙ ይገኛሉ።
እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ከሆነ ከአጠቃላይ የጋዛ ነዋሪዎች መካከል 1.9 ሚሊየን ወይም 90 በመቶው በ15 ወሩ ጦርት ከመኖሪያቸው ለመፈናቀል ተገደዋል።