![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/06/273-184228-whatsapp-image-2025-02-06-at-5.05.12-pm_700x400.jpg)
ለርስታች የህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል የማይሰስቱት ፍልስጤማውያን ከጋዛ ይለቃሉ?
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋዛን ከእስራኤል ተረክበው "የመካከለኛው ምስራቅ ሪቬራ" አደርገዋለሁ ብለዋል።
የቀድሞው የሪል ስቴት አልሚ የፈራረሰችውን ጋዛ ወደ "የአለማችን ወብ ስፍራ" እቀይራለሁ እቅዳቸው ውግዘትና ነቀፌታው ቢበዛበትም ገፍተውበታል።
ጦርነት ስለሚፈራረቅበት፤ ፍልስጤማውያን በማያባራ ጦርነት ስለሚሰቃዩበት "የአለማችን ትልቁ ክፍት እስርቤት" እየተባለ የሚጠራው ጋዛ የተሸከመው ሃብት የትራምፕን ትኩረት ሳይስብ አልቀረም።
ጋዛ ታሪካዊ የደቡባዊ ፍልስጤም ከተማ ናት፤ "ጋዛ ሃሸም" እየተባለችም ትጠራለች። ለዚህም መነሻው የነብዩ መሀመድ አያት ሀሸም ቢን አብድ ማናፍ መቃብር በጋዛ ስለሚገኝ ነው።
የጋዛ ሰርጥ 41 ኪሎሜትር ይረዝማል፤ ስፋቱ ከ6 እስከ 12 ኪሎሜትር ይደርሳል። አጠቃላይ ስፋቱም 360 ስኩዌር ኪሎሜትር ነው።
በጋዛ የባህር ዳርቻ በፈረንጆቹ 1999 የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መኖሩ ተረጋግጧል። ይሁን እንጂ ፍልስጤማውያን ከዚህ ሀብት መጠቀም አይደለም የሰላም አየር መተንፈስ አልቻሉም።
ከጋዛ ህዝብ ከሁለት ሶስተኛ በላዩ የምግብ እርዳታ ጠባቂ ነው፤ የቅርብ ጊዜው ጦርነት አብዛኞቹን ለረሃብ አጋልጧል። የጋዛ ሰርጥ በአንድ ወቅት "የፍልስጤም የምግብ ቅርጫት" ተብላ ትጠራ ነበር።
የጋዛ ሰርጥ በአለማችን ህዝብ እጭቅ ብሎ ከሚኖርባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው። ከ2 ሚሊየን በላይ ሰዎች በጋዛ ይኖራሉ፤ ከዚህ ውስጥ 1 ነጥብ 7 ሚሊየኑ ከሌላ አካባቢ የተፈናቀሉ ናቸው።
እስራኤል በጋዛ አምስት ዋና ዋና ጦርነቶችን አካሂዳለች። ሃማስ በእስራኤል ላይ በጥቅምት 2023 ያልተጠበቀ ጥቃት ካደረሰ በኋላ የጀመረችው ጦርነት ግን ከሁሉም የከፋውን ውድመት አስከትሏል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የትራምፕን ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማስወጣት እቅድ አወድሰዋል። የሀገሪቱ ጦር ከጋዛ በፈቃደኝነት መውጣት የሚፈልጉ ፍልስጤማውያንን ለማስተናገድ እቅድ እንዲያዘጋጅ ታዟል።
ርስታቸውን አስጠብቀው ለመቆየት ውድ ህይወታቸውን ለመስጠት የማይሰስቱ ፍልስጤማውያን ግን "ነፍሳችን ቢያስከፍለንም ከጋዛ ለቀን አንወጣም እያሉ ነው። የትራምፕ እቅድ ይሳካ ይሆን?