
የሴት ቢሊየነሮች አጠቃላይ ሀብት ካለፈው አመት በ240 ቢሊየን ዶላር አድጎ 1.8 ትሪሊየን ዶላር ደርሷል
ሊጠናቀቅ ሶስት ሳምንታት ብቻ በቀሩት 2024 141 አዳዲስ ቢሊየነሮች የፎርብስን የአለማችን ባለጠጋዎች ዝርዝር ተቀላቅለዋል።
የቢሊየነሮች ቁጥር ወደ 2 ሺህ 781 ከፍ ብሎ አጠቃላይ ሀብታቸውም 14 ነጥብ 2 ትሪሊየን ዶላር ደርሷል።
በ2024 የፎርብስ የቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት ውስጥ 369ኙ (13.3 በመቶው) ሴቶች ናቸው።
ከነዚህ ውስጥ 46ቱ በዚህ አመት ዝርዝሩን የተቀላቀሉ ሲሆን፥ የሴቶቹ ቢሊየነሮች አጠቃላይ ሀብት በ240 ቢሊየን ዶላር አድጎ 1.8 ትሪሊየን ዶላር መድረሱን የቢዝነስ ኢንሳይደር ዘገባ ያመለክታል።
ሴት ቢሊየነሮች በፋይናንስ፣ ችርቻሮ ንግድ፣ በአልባሳት እና ማምረቻ ዘርፍ ተሰማርተዋል።
አሜሪካ በሴት ቢሊየነሮች ብዛት ቀዳሚዋ ስትሆን፥ ቻይና፣ ጀርመን እና ጣሊያን ይከተላሉ።
በርካታ ሴት ቢሊየነሮች የሚገኙባቸውን ሀገራት ይመልከቱ፦